በሀገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ዙሪያ የ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

በሀገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በሀገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ግንቦት 5/2017 (አአ ሰፀአ ቢሮ)

*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በሀገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ከተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገር በቀል እውቀት፣ ግጭት አፈታትና የቆዩ የአብሮነት እሴቶችን በማዳበር ዘመናዊ አሰራርን ማሳደግ እንደሚገባ በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል።

አቶ ኤልያስ ቀጀላ የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ በድን መሪ ሰነዱን በዝርዝር አቅርበዋል።

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንዳሉት ሀገር በቀል እውቀትን በማሳደግ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴን በመከተል የሰላም እሴትን በማስረጽ ለትውልድ ማቆየት ይቻላል ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ አክለውም ልማትን ለማፋጠን፣ ሰላምን ለማጎልበት፣ አብሮነትን ለማሳደግና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሀገር በቀል እውቀት መነሳት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ለአብነት የጋሞ አባቶችን አኩሪ ባህልና ወግ አንስተዋል።

በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ አቶ ተስፋዬ ጫኔን ጨምሮ የክፍለ ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ

የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የሴቶችና የወጣት አደረጃጀት ተወካዮች ተገኝተዋል ።