



ሀገራዊ ማንነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
ሀገራዊ ማንነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
ግንቦት 7/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)
*******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀገራዊ ማንነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በግንዛቤው ማስጨበጫ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንደተናገሩት ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሆናችሁ በዕድለኝነት ብቻ የሚገኘውን ውድ በጎ ስራ ተቀብላችሁ ወደ ተግባር በመቀየራችሁ ምስጋና ይገባችኋል ነው ያሉት ሀላፊው
ሀገር የሰጠቻችሁን አደራ ተግባራዊ በማድረግ በኩል ሀላፊነታችሁንም እንድትወጡ አደራ እላለው ያሉት ሀላፊው ሀገራዊ መግባባት ላይ አንድነትን በመፍጠር ሀገረ መንግሥት በጋራ በመምራት የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በአንድነት ልንገታ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል
ሀላፊው አክለውም ኢትዮጵያ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገኛ በርካታ ሀይማኖት በአንድነት የሚኖሩባት ድንቅ ሀገር ነች ብለዋል።
በልዩነት ውስጥ አንድነትን አጠንክረን የምንኖር ሰዎች እንደመሆናችን ጭምር በመከባበር፣ በመተሳሰብና በመፈቃቀር የምንኖሩባት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።በመጨረሻም አገርን ከሚፈትኗት ችግሮችን አስቀድሞ በመረዳት የተጣለብን ሀላፊነት መወጣት ይገባናል ሲሉ ተደምጠዋል ።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ኤልያስ ቀጄላ የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስልጠና ቡድን መሪ ሲሆኑ የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደትን ለአሁኑ ትውልድ በተገቢው መንገድ መስተማር ይገባልም በማለት በሰነዱ አመላክተዋል።
በስልጠናው ላይ አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣ የሁሉም ክ/ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና የ12ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል ።