



አዲስ ለተደራጁ የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ ለተደራጁ የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ግንቦት 6/2017 (አአ ሰፀአ ቢሮ)
*******
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አዘጋጅነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በአዲስ ለተደራጁ የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ
አንቀሳቃሾች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠናው ትኩረት በቅድመ-ወንጀል መከላከል፣ በሀገር ወዳድነት፣ በስነ-ምግባርና በስሜት ልህቀት ዙሪያ መሆኑ በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል።
በከተማ ደረጃ በ6 የስልጠና ማዕከላት የስራ እድል ተጠቃሚ ወጣቶች በትኩረት እየተከታተሉና የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።