ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ውይይት ተካሄ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ ።

ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሁናዊ የከተማውን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አድርጓል ።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት አገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ለውጥ ውስጥ ያለች አገር እንደመሆኗ መጠን አልፎ አልፎ ለዉጡን ተከትለው የሚከሰቱ የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ችግሮቹን በማለፍ ትላልቅ ድሎችን ማስመዝገብ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

እንደ ጸጥታ መዋቅርም ከተማችን ያለችበትን የፀጥታ ሁኔታ በየጊዜው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ወቅታዊ ሁኔታዎቹን መሰረት ያደረጉ የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን በመከተል ምላሽ የምንሰጥ በመሆኑ መድረኩ ከዚህ አንፃር የሚታይ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ሚደቅሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው በከተማው ላይ በየግዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን ከስሩ ለመግታት እየተሰራ እንደሆነ ሁሉ ወንጀልን በመከላከል በመቆጣጠርና የጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎች ሴራ የማክሸፍ ስራው በቅንጅትና በንቃት በመስራት የመጣ ውጤት ነው፡፡ወደፊትም የባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት፤ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ባለቤት በማድረግ መልካቸውን በመቀያየር አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን መቀነስ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል ።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።

See translation