ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ስል...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ሰኔ 9/2017( አአ ሰፀአ ቢሮ)

******

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው ።

የስልጠናው አላማ ቢሮው የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር በመቀየር ወቅታዊ፣ተደራሽና ጥራት ያለው አሰራር ለመዘርጋት መሆኑም በቀረበው ሰነድ ተብራርቷል።

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እንዳሉት የቴክኖሎጂ ስራ ዓለም አቀፍ መሆኑን ጠቅሰው በጥራት በፍጥነትና ዘመናዊነትን በተከተለ መንገድ ውጤታማ ለመሆን ቴክኖሎጂን በአገባቡ መጠቀም ይገባናል ብለዋል።

የቢሮው ሁሉም ሰራተኞች ስልጠናውን በተገቢው መንገድ በመከታተል የተለመደውን አሰራር በመቀየር፣ራስን በማብቃት ተወዳዳሪነትን በማሳደግ እንዲሁም በመደጋገፍ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ስልጠናው ቀጣይነት እንዳለው የተገለፀ ሲሆን በዛሬው ዕለት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የአይሲቲ ቡድን መሪ አቶ አበበ ተካና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ በዘመናዊ የንብረት አያያዝና ምዝገባ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።