ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ሲሰ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ቢሮው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ሰኔ 10/2017( አአ ሰፀአ ቢሮ)

******

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች

ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

ስልጠናው በሰው ሃብት እና በንብረት አስተዳደር ዙሪያ በቢሮው የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር በመቀየር ወቅታዊ፣ተደራሽና ጥራት ያለው አሰራር ለመዘርጋት መሆኑንም በቀረበው ሰነድ ላይ ተብራርቷል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እንዳሉት ቢሮው የቀድሞ የተንዛዛ አሠራርን በማስቀረት በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሠራር በመተካት ጊዜ፣ጉልበትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ ዕርካታን ለማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው በሁለት ዙር የተሠጠ ሲሆን ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ቢሮ የመጡ ባለሙያዎችና እንዲሁም የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአይሲቲ ቡድን መሪ አቶ አበበ ተካ ስልጠናውን ሰጥተዋል።