ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ90 ቀናት እቅድ

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ90 ቀናት እቅድ

"ማህበረሰቡን ያሳተፈ የተጠናከረ የፀጥታ ስራ በ90 ቀናት እቅድ ተግባራዊ ይደረጋል"።

* ክብርት ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

ሰኔ 10/2017 (አአ ሰፀአ ቢሮ)

በዘጠና ቀናት እቅድ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሰላም ባለቤት በማድረግ የተጠናከረ የፀጥታ ስራ እናከናውናለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ሊዲያ ግርማ አስታወቁ።

በዛሬው ዕለት የከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ90 ቀናት የማስፈፀሚያ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የስራ አቅጣጫ ሰጥቷል።

ተሳታፊዎችም እቅዱ ወቅታዊና የሚያሰራ መሆኑን አንስተው በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት አለብን ሲሉ አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት ማህበረሰቡን ያሳተፈና ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት ያደረገ በቅንጅት የሚመራ የፀጥታ ስራ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቅሰው በበጎ ፈቃድ ስራዎች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በትኩረት በመስራት እቅዳችንን ማሳካት አለብን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪምበኮሪደር ልማት ደህንነት፣ለሀገራዊ ምክክርና ለህዝባዊ ውይይት መድረኮች መሳካት እንዲሁም ለሰላም ሰራዊት መጠናከርከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንሰራለን ሲሉ አስምረውበታል።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በኢኮኖሚ አሻጥር፣ በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት፣ በህዝባዊና ብሔራዊ በዓላት አከባበር እንዲሁም በንቅናቄ ስራዎች 7/24 በመስራት በዘጠና ቀናት የተቀመጠውን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር ቁርጠኛ መሆን አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዘጠና ቀናት እቅድ ክንውን በሪፖርት፣በድጋፍና ክትትል እንዲሁም በተግባር ምልከታ መምራት፣የከተማውን የፀጥታ አዝማሚያን በሚገባ መተንተንና መተንበይ፣

ሕብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ፣

የማሕበረሰብ አቀፍ ውይይትን አጠናክሮ ማስቀጠል ወዘተ..በክብርት የቢሮ ኃላፊዋ ዝርዝር አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ሊዲያ ግርማን ጨምሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣የማዕከል ዳይሬክተሮች፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።