የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017ዓ.ም በጀት ዓ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ90 ቀናት ዕቅድ

የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ ።

ሰኔ 12/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች፤ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር ውይይት አድርጓል ።

በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የዘርፉ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በጋራ አቅምን በማጎልበት ወደ ስራ ከገባን በኃላ እንደ ዘርፍ ስኬታማ የሆንበት ቢሮውን ከፍ ያደረገ ስራ ተሰርቷል ካሉ በኃላ ስራው ህብረተቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንደተቻለ፤ የወንጀል ምጣኔም 43 በመቶ መቀነስ እንደተቻለና የሰላም ሰራዊት አባላትን በመመልመል በማደራጀትና ወደ ስራ በማስገባትም ከተማው ላይ የጸጥታ አጋዥ ኃይል በማድረግ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው ህብረተሰቡ የጸጥታ አጠባበቁ እንዲጎለብትና ችግሩን በራስ አቅም እንዲፈታ ማድረግ መቻሉ በጋራ ጥረት የመጡ ውጤቶች ናቸው ብለዋል፡፡

የህብረተሰብ ንቅናቄ ስራዎችን በመስራት የሰላሙ ባለቤት በማድረጋችን በከተማው ላይ የተካሄዱ፤ባህላዊ፤ብሔራዊ፤አህጉራዊና አለማቀፋዊ ኮንፍረንሶችና ጉባኤዎችን በሰላም ማክበር መቻሉ ማሳያ ከመሆናቸውም በበለጠ የጥንካሬዎቻችን መገለጫዎች ቢሆኑም እንቅፋት የሆኑ ነገሮች አልነበሩም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ዘርፉ በነበረው አስተዋጽኦ የጠላት ሴራን ማክሸፍ እንደተቻለም ሀላፊው ጠቁመው ባለፈው በጀት ዓመት በስኬት የተወጣናቸውን ተግባራት በማጠናከር፤ ያላጠናቀቅናቸውን ሥራች ሌት ተቀን በትጋት በመስራት የዘጠና ቀናት ዕቅዶቻችንን በስኬት ለመፈፀም ዝግጁ መሆን ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል ።

ሶስት ክ/ከተሞች ማለትም አራዳ፣ኮልፌና ልደታ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን አቶ ውድነህ አቢ የቢሮውን የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የዕቅድና ሪፖርት ዶ/ር ፍሬ ህይወት በለጠ ደግሞ የዘጠና ቀናት ዕቅድ ሪፖርቱን በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ።

በውይይቱ ላይ የዘርፉ የማዕከል ባለሙያዎችና የሁሉም ክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል ።