







4ኛ ሩብ ዓመት ክትትልና ድጋፍ ግብረ-መልስ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ ።
የ2017 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት ክትትልና ድጋፍ ግብረ-መልስ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ ።
ሰኔ 13/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ የ2017 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት ክትትልና ድጋፍ ግብረ-መልስ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች፤ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር ውይይት አድርጓል ።
በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የዘርፉ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደተናገሩት ቢሯችን የከተማችን ሰላምና ደንነት ለመጠበቅ እና ወንጀልን በመከላከል ረገድ በርካታ ስራ የሰራ ሲሆን ዘርፋችንም ለዚህ ቁልፍ ተግባራት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በሰላም ግንባታ ዙሪያ በተሰጠው ግንዛቤ ማስጨበጫ ህብረተሰቡ በራሱ የሰላም ባለቤት ከመሆን አልፎ ለሌሎች ሰላም መስፈን አስተዋጽኦ ማድረግ ችሏል ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ 90ቀናት ውስጥ በብሄራዊ በጎፍቃድ ስምሪት በመስጠት የተሻለ ስራ መስራት፣ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ንቅናቄ፣ ኮንፍራንስ እና ህብረተሰብ ተኮር ውይይቶች በመካሄድ የነበረውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በመሙላት የከተማችንን ሰላም ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የዘርፉ የ4ኛ ሩብ ዓመት የክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ ሪፖርትና የ90 ቀናት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት በምክትል የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቷል።