በሙስና ምንነትና ማምከኛ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በሙስና ምንነትና ማምከኛ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።

የቢሮው የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በሙስና ምንነትና ማምከኛ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በሙስና ምንነትና ማምከኛ ስልቶች ዙሪያ ለቢሮው የወረዳ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ገብሬ ዳኘው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እንዳሉት ባለፈው በጀት አመት ቢሮው ህግ አስከባሪ እንደመሆኑ መጠን ከፀረ-ሙስና ጋር በተያያዘ ሌብነትና የብልሹ አሰራር ለመከላከል በርካታ ስራዎች መስራቱን እና የብልሹ አሰራር ጎጂነት በማወቅ ለከተማችን ልማት እንቅፋት እንዳይሆን በማድረግ ረገድ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት መቻሉን ገልጸው፤ አሁን ከዚህ ስልጠና በኃላም ሰልጣኞች ያገኙትን ግንዛቤ ለሌሎችም በማስገንዘብ እራሳቸውንም ከሙስና በማራቅና ብልሹ አሰራርን በመታገል የከተማቸውን ሰላም እና ልማት ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የስልጠናው አላማ ሙስና ሳይፈጸም በፊት የሚከሰተውን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል፣ እራስን ከሙስና ለማራቅ እና ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ነው ተብሏል።

ሥልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና የፀረሙስና ተቋም በመጡ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በሰነዱም በሙስና ምንነት፣ ልዩ ባህሪያት፣ አይነቶቹ፣ መገለጫዎቹ፣ የጥቅም ግጭቶችና ከስልጠናውም በኃላ ስለሚጠበቁ ውጤቶች በዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።