ለ13ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ ፍቃደኞች አቀባበል ተደረገላቸው።
ለ13ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ ፍቃደኞች አቀባበል ተደረገላቸው።
ሰኔ 23/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
********
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ለ13ኛ ዙር ቢሄራዊ በጎ ፍቃደኞች አቀባበል አድርጎላቸዋል።
በጎ ፈቃደኞቹ ከደቡብና ኦሮሚያ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸው ታዉቋል፡፡
መረሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ሙሉቀን እንየው እንዳሉት ይህ የቢሄራዊ በጎ ፍቃድ አንዱ ለአንዱ የአከባቢውን ቋንቋ፣ ባህልና እሴት ለመጋራት ስለሆነ ለብሄራዊ አንድነትና ለአገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ለማህበረሰቡ በራስ ፍላጎትና ተነሳሽነት በነፃ አግልግሎት የመስጠት ባህልን የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል።
"መልካምነት ለራስ ነው" እንደሚባለው ሁሉ ማህበረሰቡን በመጥቀማችሁ ትልቅ የህሊና ዕርካታን የሚታገኙበት ስራ ነውም ብለዋል ዳይሬክተሩ።
የበጎፍቃድ ስራ በተመለከተ የብሄራዊ በጎ ፍቃድ መነሻ ሃሳብ፣ የባለድርሻ አካላት ሚና እና ለሃገርና ለማህበረሰቡ ያለው ጥቅሜታ የያዘ ሰነድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።