ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን የ2017 ዓመታዊ እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን የ2017 ዓመታዊ እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

ሰኔ 26 /2017 (አአሰፀአ ቢሮ)

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከደንብ ማስከበር ባለስልጠን ጋር በመሆን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

በዕለቱ የሁለቱም ተቋማት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የለውጥ፣ የዲፕሎማሲና የልማት ከተማችንን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ፤

ግብና አላማ አስቀምጠን፤በእቅዳችን መሰረት ከህዝቡ ጋር በመስራታችን፣አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ወንጀልን በመቀነስ፣ ብሔራዊና ኃይማኖታዊ በዓላት በሰላምና በፍቅር እንዲከበሩ ከማድረግ አንጻር፣ የደንብ መተላለፍን ቀድሞ በመከላከል በተጨማሪም በአርቲፍሻል የዋጋ ጭማሪ ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ በበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ስኬታማ ተግባር ተከናውኗል።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በትራንስፖርት ስምሪትና ህጋዊ ማዕቀፍ በመዘርጋት፣የጽንፈኝነት አዝማሚያን በመረዳት ህጋዊ እርምጃን በመውሰድ፣ለበጀት ዓመቱ እቅድ መሳካት ቅንጅታዊ አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንደነበረው ጠቅሰው በደንብ መተላለፍ በህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ፤ በመሬት ወረራ በኮሪደር ልማት ጥበቃ በሰው ኃይል በማጠናከር በ2017 በጀት ዓመት ትልቅ ስራ ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይም ይህንን ተግባር አጠናክረን በመቀጠል ለውጤት መብቃት አለብን።

ጥንካሬን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም እንሰራለን በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጠን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች በትኩረት ተለይተው መገምገማቸው ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው ለ2017 እቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት የተቋም ግንባታችን ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ብለዋል።

የከተማዋን ህብረተሰብ የሰላሙ ባለቤት በማድረግ፣የኮሪደር ልማትን በመጠበቅ እንዲሁም የሰላም ሰራዊትን በማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን በማስፋትና የ2018 እቅድን እየገመገሙና በቴክኖሎጂ እያስደገፉ መስራት ለበለጠ ስኬት ያበቃናል።

ሻለቃ ዘሪሁን አክለውም ዘጠኙን የደንብ መተላለፎችን አስመልክቶ ግንዛቤ በመፍጠር፤ ቀድሞ በመከላከልና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግባል።

በግምገማዊ ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፤ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት ተወካዮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።