የቃል ግብረ-መልስ

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቃል ግብረ-መልስ

በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ምልከታ ላይ የቃል ግብረ-መልስ ተሰጠ።

ሰኔ 27/2017ዓ/ም ( አዲስ አበባ)

*******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በግብረ-መልሱ ወቅት እንዳሉት የሱፐር ቪዥን ቡድኑ ያደረገው የሱፐርቪዥን ሥራ አቅም ሊሆን የሚችል ሲሆን፣አሁን ቢሮው ያስመዘገባቸውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል ክፍተቶቹን ሞልቶ የላቀ አፈፃፀም ላይ ለመድረስ እንድንሠራ ያግዘናልም ብለዋል።

በከተማ ደረጃ የተዋቀረ ሱፐርቪዢን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የመንግስት ሥራ አፈፃፀም ላይ ምልከታ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና የቢሮው አፈፃፀሞች ሪፖርት በሱፐር ቪዥን ቡድኑ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

የሱፐርቪዥኑ ቡድኑ በምልከታው ከሰላም አንጻር በተለይም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ፣አደረጃጀቶቹን በመፍጠር ወጣቶቹን በማህበራት በማደራጀት የሰላም አጋዥ ኃይል እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር፣የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሠጣጥ ሥራዎች፣ድጋፍና ክትትል ከማዕከል እስከ ወረዳ የማድረጉ ስራ በጠንካራ ጎን ከሚጠቀሱ መካከል ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፣በክፍተት የተስተ

ዋሉ ጥቃቅን ጉዳዮች በቀጣይ እንዲስተካከሉ በግብረ-መልሱ ወቅት አንስተዋል።

የሱፐርቭዥኑ ቡድን በበጀት አመቱ አጠቃላይ የተሰሩ የመንግስት ሥራዎችን ከዕቅድ እስከ ተግባር ያለው ክንውን የሚያበረታታ እንደሆነም ጠቁመዋል።