በ2017 በጀት ዓመት የ11ዱ ክ/ከተሞች በድጋፍ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በ2017 በጀት ዓመት የ11ዱ ክ/ከተሞች በድጋፍና ክትትል እንስፔክሸን ግኝትና በ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

በ2017 በጀት ዓመት የ11ዱ ክ/ከተሞች በድጋፍና ክትትል እንስፔክሸን ግኝትና በ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

ሐምሌ 02/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

********

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ11ዱ ክ/ከተሞች ድጋፍ፣ክትትልና እንስፔክሸን ግኝት ሪፖርትና በ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደን ጨምሮ ከክ/ከተማ እስከ ወረደ የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች፣አስተባባሪዎች እና የዴታቤዝ መዝጋቢዎች በተገኙበት ነው።

በእንስፔክሸን ግኝት ሪፖርት፣የ90 ቀናት እቅድ ፣የህዝብ ቅጥር ጥበቃ እና የሰላም ሰራዊት አባላት መረጃን በተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በሰነዶቹም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቅናቄ መድረኮች መካሄዳቸው፣ ማህበረሰብ ተኮር ውይይት እንዲሁም የሰላም ሰራዊት አባላት ምልመላ ሴቶች እና ወጣቶችን ያሳተፈ መሆኑ ከተገለጹት ጠንካራ ጎኖች መካከል ጥቂቶቹ ሲሆኑ በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች የመረጃ አያያዝ ክፍተቶች የተስተዋሉ በመሆኑ በቀጣይ ማስተካከል እንደሚገባ በሪፖርቶቹ ተጠቅሷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እና የቢሮው ምክትልቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ ሲሆኑ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ በዚህን ጊዜ እንደተናገሩት የሰላም፣የፀጥታና የደህነነት ስራ ራስን መስጠት፣ በውስጣዊ ስሜት፣በትጋትና በፅናነት መስራትን የሚፈልግ ነውና የፀጥታ ተቋም አመራርና ባለሙያ ሁል ጊዜ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ያገናዘበ ዝግጅት ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።

ክብርት የቢሮ ኃላፊዋና አቶ ሚደክሳ ከበደ በቀረቡት ሪፖርቶችና ሰነዶች ላይ ተሳታፊዎችን ካወያዩ በኋላ ሕብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግን ማስቀጠል፣የሰላም ሠራዊቱንና የቅጥር ጥበቃውን ማነቃቃትና በሰው ኃይል ማጠናከር ወዘተ... ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲደረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተሰጥተዋል።