በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የማጠ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የማጠቃላይ ውይይት ተካሄደ

በበጀት ዓመቱ የታየው የወንጀል ምጣኔ መቀነስ በመዋቅሩ ውስጥ የሚገኙአመራሮች፤

የባለሙያዎች፤የህብረተሰቡ ተሳትፎና የፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት መሆኑ ተገለፀ ።

ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)

*******

ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የማጠቃላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

በበጀት አመቱ ከቢሮው ዕቅድ አንፃር የተከናወኑትን ተግባራትና ግብ ስኬቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተለያዩ ግዜያት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በመፍጠር፤የማህብረተሰብ ተኮር ውይይት በማድረግ፤ የጸጥታ ስጋት ቦታዎችን በመለየት ፈጣን ምላሽ በመስጠት፤የጸረ ሰላም ሀይሎችንና ህገ-ወጥ የኢኮኖሚ አሻጥር ድርጊቶችን መከላከልና መቆጣጠር፤ከተማውን የሚመጥን የትራንስፖርትና የተርሚናል አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊማድረግ፤

ሃይማኖታዊና ባህላዊ፤በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በማድረግና በአጠቃላይ በከተማው ላይ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና ሰላም የሰፈነባት ከተማ ማድረግ መቻሉን በቀረበው ሪፖርት ላይ እንደ ስኬት የተጠቀሱ ናቸው፡፡

በግምገማዊ ውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑት ተግባራትና የመጡ ለውጦች በሙሉ በመዋቅሩ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በህብረተሰቡ ተሳትፎና የፀጥታ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም አዲስ አበባ ከተማ ትልቅና እንደ ስሟ አዲስ እየሆነች የመጣች፤ሰለምና ደህንነቷን ያፀናች ከተማ ናት ይህን ለውጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቅብናል ሲሉ ተደምጠዋል ።

አቶ ተሻለ አክሊሉ የቢሮው የጽ/ቤት ሀላፊው በበኩላቸው የቢሮው የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም እያደገ በመምጣቱ በዚያው ልክ ውጤማና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን ማስቀጠል ይገባናል፤የሰላምን ጠቀሜታ ህብረተሰቡ በሚገባው ስለተረዳ ተሳታፊነቱ በእየጨመረ መጥቷል፡፡ይህን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተሳትፎውን ማጎልበት አዲስ የመመልመል፤የማሰልጠንና ስምሪት የመስጠት ጥረታችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡