ጨለማን ወደ ብርሀን የቀየሩ ሞዴል ብሎኮች እና ቀጠናዎች የጉብኝት መርሐ ግብር
ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የጸጥታ ሥራ በመሠራቱ በከተማዋ ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጡን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ገለጹ።
ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
********
በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጨለማን ወደ ብርሀን የቀየሩ ሞዴል ብሎኮች እና ቀጠናዎች የጉብኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ማኅበረሰቡን በማሳተፍ በከተማችን ዘላቂ ሰላምንበማረጋገጥና ወንጀሎች ከመከሰታቸው በፊት በመከላከል በኩል ዘርፈ ብዙ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
በከተማዋ የወንጀል ምጣኔ 43 በመቶ መቀነሱን ያብራሩት ኀላፊዋ ጨለማን ተገን አድርገው የሚፈጸሙ ወንጀሎች በመቀነስ ደረጃ ማኅበረሰቡ ስታንዳርዱን የጠበቀ መብራት በየብሎኩ እንዲያወጣ መደረጉን እና የኢዲስ አበባ የኤሌትሪክ አገልግሎት ለረዥም ጊዜ ጠፍተው የነበሩ የመንገድ ዳር መብራቶችን በመጠገን ረገድ በክፍለ ከተማው ለሌሎች ክፍለ ከተሞች ተሞክሮና ልምድ የሚቀሰምበት ሥራ መሥራቱን ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ አንደገለጹት የክፍለ ከተማውን ሕብረተሰብ ባሳተፈ መልኩ የሰላምና ጸጥታ ተግባራት መከናወናቸውን ያነሱ ሲሆን በክፍለ ከተማው በሚገኙ 448 ብሎኮች መብራት በማስበራት ሞዴል የጸጥታ ብሎኮች መፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
የክፍለ ከተማው የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ በበኩላቸው ሕብረተሰቡ መብራት እንዲያወጣ በ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ በተሠሩ የንቅናቄ ሥራዎች ከ17 ሺህ በላይ አባወራዎችና እማወራዎች መብራት ማውጣታቸውን ጠቁመው ድምር ውጤቱም ወንጀልንና ስጋትን እንደሚቀንስ አብራርተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ፣ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ኮሚሽነር ፍቅሩ ዓለማየሁ የኢዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ም/ኮሚሽነር፣የአዲስ አበባ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ጸሀይ ኪባሞ ፣የከተማና የክ/ከተማ አመራሮች፣እንዲሁም የ11ዱም ክፍለ ከተሞች የፖሊስ መመሪያ ኃላፊዎች፣የደንብ ማስከበርና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።