በመስከረም ወር የሚካሄዱ የአደባባይ በዓላት የፀ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በመስከረም ወር የሚካሄዱ የአደባባይ በዓላት የፀጥታ ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ዉይይት

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመስከረም ወር የሚካሄዱ የአደባባይ በዓላት የፀጥታ ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ከማእከል እስከ ወረዳ ካሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች ጋር የጋራ አደረገ።

                                                                ***

                                                መስከረም 07/2018 ዓ.ም

ቢሮዉ በ2018 ዓ.ም በተያዘው የመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሐይማኖታዊና ባህላዊ ትዉፊታቸዉን ጠብቀዉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረዉ እንዲጠናቀቁ በማለም የፀጥታ ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ከማእከል እስከ ወረዳ ካሉ የሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የደንብ ማስከበር አመራሮች እና ዳይሬክቶሬቶች ጋር የጋራ በማድረግ ዉይይት አካሄዷል።

ወይይቱን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ እና ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ናቸዉ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ዉይይቱን በመሩበት ወቅት እንደገለፁት ቢሮዉ ከመስከረም 01 ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የነበሩ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሁነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ ከመላዉ ጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት እቅድ አቅዶ ወደ ተግባር የገባ መሆኑን አዉስተዉ፤ የዛዉ አንድ አካል የሆነ የማስፈጸሚያ እቀድ የመስቀልና የኢሬቻ ቱባ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ትዉፊታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ ከባለፈዉ አመት ተሞክሮ በመዉሰድ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ለመወያየት የተዘጋጀ መድረክ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

ኃላፊዋ አክለዉም ከባለፈዉ አመት ባማረ መልኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚፈጥሩ የመስቀልና የኢሬቻ ዓላት እንደየ ፋይዳቸዉ ተከብረዉ እንዲጠናቁ ጠንካራ ስምሪት ዉስጥ ገብተን የጸጥታ ግብረሃይሉ በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም ህዝብን ከጎናችን በማሰለፍ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸዉ ተግባራት የተሻለ ተሞክሮ ያገኘንበትና ህብረተሰቡ የመስቀልና ኢሬቻ በዓልን በደስታ አክብሮ የተመለሠበት በመሆኑ ያንኑ ለማስቀጠል እና በከተማችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰፋፉ ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎችን የሠራንበት፣የህዝቡን ተጠቃሚነት አጉልተን ያሳየንበት፣ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር እጅ ለእጅ የተያያዘበት እና በተለይም የህዳሴ ግድባችን መመረቅ ለማህበራዊ፣ለኢኮኖሚያዊና ለፓለቲካዊ እንቅስቃሴያችን የፈጠረዉን መነቃቃት ለማወክና የህዝቡን ደስታ ወደ ሀዘን እንዳይቀየር የጸጥታ መዋቅሩ ሁኔታዎችን በመረዳት በቅንጅት መሠራት እንዳለበት ጠቁመዉ፤ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሳተፉ ህዝቦች ያሉበት የኢሬቻ በዓል በየ መግቢያ በሮቹ የሚሰራዉ የጸጥታ ስራ ጠንከር ያለ መሆን እንዳለበት አንስተዋል።

የበዓል የፀጥታ ስራ ማስፈጸሚያ እቅዱን ያቀረቡት በአቶ ማስረሻ ሀብቴ አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ፣ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ፣የሰላምና ጸጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ ፅ/ቤት

ኃላፊዎች እንዲሁም የክ/ከተማ የዘርፎች ስራ ሂደቶች ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ላይ ከመድረኩ አወያዮች ምላሽ ተሠጥቶ፤ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ ህዝቡን ባለቤት በማድረግ ከመላዉ የጸጥታ መዋቅር የሚጠበቁ ተግባራትን በዝርዝር በቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ዉይይቱ ተጠናቋል።