በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የሸገር ከተማ ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት መካከል ህግ በማስከበር ዘላቂ ሰላም በጋራ ለማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የሸገር ከተማ ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት መካከል ህግ በማስከበር ዘላቂ ሰላም በጋራ ለማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መስከረም 13/2018 ዓ.ም (ሸገር)
የዚህ መድረክ ዋና ዓላማውም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት ከሸገር ከተማ ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በከተማው የፀጥታ መስፈን ስራዎችን በቅንጅት፣በትብብር እና በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ዘላቂና ተቋማዊ በሆነ መንገድ የከተማቹን ሰላም፣ፀጥታና ደህንነት ማስፈን ማስቻል እንደሆነም ጠቁመዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የሸገር ከተማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ በኃላ የህዝቦችን ደህንነት፣በሰላም ወጥተው መግባት የማህበራዊ ሰላም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በጋራ አጠናክሮ በማስቀጠል ረገድ አሁን ያለውን ውጤት ለማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው ከተማችን አዲስ አበባ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር ለተከታታይ 3 ዓመታት የህብረተሰብ ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራሮችን የበለጠ በማጎልበት እና ተቋማዊ አሰራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል፣በትብብር በመስራታቸው ታላላቅ ሀይማኖታዊ፣ባህላዊና መንግስታዊ የአደባባይ በዓላትና ኩነቶች በሰላም እንዲከበሩ የማድረግ ስራና እንዲሁም የሽብርና ጽንፈኛ ሀይሎች በሌሎች የወንጀል ድርጊቶችን በግልም ሆነ በቡድን የሚሳተፉ ሀይሎች ላይ በቅንጅት በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
ሀላፊዋ አክለውም ከፊታትን የሚከበሩ የሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላቶች፣ትውፊታቸውንና ዕሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከሸገር ከተሞች ጋር በቅንጅትና በጋራ እየተሰራ እንደሆነና በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም አመላክተዋል።
ለመድረኩ መወያያ መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡ የቢሮው የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ሲሆኑ፣በገለጻቸው ወቅትም ወቅታዊ ሁኔታዎች ለፀጥታ ስራ ያላቸው እንድምታ፣የሁለቱም ከተሞች ህዝብ ሁኔታን እንዲሁም ዋና ዋና ግቦችና የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እና የአፈፃፃም አቅጣጫዎችን በሰነዱ አብራርተው አቅርበዋለ።
በመድረኩም ላይ የሸገር ሲቲ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮምሽነር ጌቱ አርጋ፣በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱም ከተሞች አመራሮች፣የሁለቱም ከተሞች ሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።