"ከጂኦ_ስትራቴጂያዊ_ኩስመና_ወደ_ታደሰ_ቁመና"...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ከጂኦ_ስትራቴጂያዊ_ኩስመና_ወደ_ታደሰ_ቁመና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።

"ከጂኦ_ስትራቴጂያዊ_ኩስመና_ወደ_ታደሰ_ቁመና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።

**

መስከረም 27/20178 (አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ውይይቱ የወደፊት እርምጃችንን የሚያሳምር አጀንዳ በመሆኑ ሰራተኛው በሙሉ ልቡ ውይይቱ ላይ መሳተፍ እንደሚገባው በመድረኩ መጀመሪያ ላይ በማሳሰብ፤ ሀገራችንን ኢትዮጵያ አብዛኞቻችን በደምብ አልተረዳናትም እንጂ በተፈጥሮ እና በሰው ሃይል እንደ ኢትዮጵያ የታደለ ሃገር አለመኖሩን አንስተው፤ ይህ ሁሉ ሀብት እያለን የድህነታችን ትልቁ ምክንያት አለመግባባታችን እና የአገራችን ፈጣን እድገቷ ህመም የሆነባቸው አገሮች አጀንዳ ቀርፀው የሚላኩ ባንዳዎችን ሳንረዳ የውስጥ ችግር ብቻ መስሎን እርስ በራሳችን መበላላታችን ነውና፤ የወደቀ የስራ ባህላችን በመቀየር እንዲሁም በሃይማኖትና በዘር ሳንከፋፈል ከግልና ከቡድን ጥቅም ይልቅ የሀገር ጥቅምን በማስቀደም በአንድነት ወደ ዲጃታል አለም በመቀላቀል ከሰራን የኢትዮጲያ ብልፅግና ቅርብ ነው ብለዋል።

የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው በበኩላቸው

ቢሄራዊ ጥቅም ከግለሰብና ከቡድኖች ፍላጎት የተሻገረ፣ የተደመረ የብዙሃን ጥቅም መሆኑ ገልጸው፤ የጋራ ጥቅም የትናንት፣ የዛሬ እና የነገ ህልውና ደህንነት እና እድገታችን የሚወስን በመሆኑ እነዚህ ድሎች ማላቅ፣ የኢኮኖሚ እድገት መፉጠን እና የባህር በር ጉዳይ መቋጨት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ድርሻ ስለሆነ ሁሉም ሚናውን መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመወያያ ሰነድን ያቀረቡት የቢሮው የስነምግባርና የጸረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ ባለፉት 7 የለውጥ አመታት ውስጥ በዋናነት ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ለውጦች በተግዳሮቶች ሳይበገሩ ማንሰራራታቸው፣ የአባይ ምንጭ በመቆጣጠር በቀጠናዊ ጂኦ ስትራቴጂያዊ የማናችንን መለወጥ መቻሉን እና የባህር በር የማግኘት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብታችንን አለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ በዚህም ጂኦ ስትራቴጂያዊ የማናችንን ለመመለስ ከአንድ ምዕራፍ በላይ መራመድ መቻሉ ጠቅሰው፤ ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ለውጥ እና የሀገር ህልውና በሰፊ አብራርተዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ከሰራተኞች ጋር ተደርጓል።