የሪፎርም ስራ ላይ ውይይት ተደረገ። **
በመስከረም ወር በከተማችን የተከናወኑ የአደባባይ ክብረ በአላት እንዲሁም አለም አቀፍና አህጉራዊ ኩነቶች እና ኮንፈረንሶች የፀጥታ ስራ አፈፃፀምን በመገምገም በቀጣይ በተቋሙ በሚደረገው የሪፎርም ስራ ላይ ውይይት ተደረገ።
**
መስከረም 27/2018 ዓ.ም (አዲስአበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማእከል እስከ ወረዳ ካሉ የቢሮዉ አመራሮች ጋር በ2018 ዓ.ም በመስከረም ወር በከተማችን የተከናወኑ የአደባባይ ክብረ በአላት እንዲሁም አለም አቀፍና አህጉራዊ ኩነቶች እና ኮንፈረንሶች የፀጥታ ስራ አፈፃፀም ሪፖርትን በመገምገም በቀጣይ ቢሮዉ በሚያካሄደዉ የሪፎርም ተግባራት ጋር ተያይዞ ውይይት አካሂዷል።
መድረኩን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፤ በ2018 ዓ.ም በመስከረም ወር የተከናወኑ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት፣ አለም አቀፍና አህጉራዊ የሆኑ ኩነቶችና ኮንፈረንሶች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በስኬት እንዲጠናቀቁ በብቃትና በቁርጠኝነት ያለምንም መሰላቸትና መታከት በመስራት ፍጹም ሰላማዊ ሆነዉ እንዲያልፉ የህዝብን አቅምና መላዉ የጸጥታ መዋቅርን በመጠቀማችን ዉጤቱን በተግባር ያየነዉ በመሆኑ ለሁሉሞ የጸጥታ መዋቅር ምስጋና ይገባል በማለት፤ቢሮዉ በሚሰራቸዉ ሌሎች መደበኛ የጸጥታ ስራዎችም ከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪዎቿ ያለምንም ስጋት ወጥተዉ እንዲገቡ በቅንጅት መስራቱ መቀጠል እንደሚገባው አዉስተዋል።
የበዓላት ስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የቢሮዉ የሪፎርም ስራዎችንና መመሪያዎችን በተመለከተ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፤ በሰነዱም አጠቃላይ ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ ሲተገበሩ የቆዩ ሂደቶችንና አፈጻጸሙን ዳሰዉ፤የቢሮዉን ሪፎርም ተግባራትን በተመለከተ በፈተና አሰጣጥ ሂደት መከናወን ያሉበትን ጉዳዮች ደንብና መመሪያዎችን ለግንዛቤ በሚሆን መልኩ አዉስተዉ ከማእከል እስከ ወረዳ መሟላት የሚገባቸዉን ቅድመ ሁኔታዎች አካተዉ አቅርበዋል።
በመድረኩም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ፣ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችና አማካሪዎች ፣የ11ዱም ክፍለ ከተማ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና አስተባባሪዎች የወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና የማእከል ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል ።
በቀረበዉ ሰነድ ላይ ሰፊ ወይይት ተደርጎበት፤በክብርት ሊዲያ ግርማ አማካኝነት ማጠቃለያ የተሠጠበት ሲሆን፤ሀላፊዋም በተነሱቱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት፤ ከዚህ ቀደም የነበረንን መናበብና መደማመጥ በመድገም ህብረተሰቡ ውስጥ የባለቤትነት ስሜት በማስረጽ ሌት ተቀን በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በእዉቀትና በመረጃ ላይ የተመረኮዘ የጸጥታ ስራዎችን ቀምሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።በመጨረሻም ሀላፊዋ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዉ ዉይይቱ ተጠናቋል።