ቢሮው እየሰራ ባለው የሪፎርም ስራ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች የፈተና ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡
ቢሮው እየሰራ ባለው የሪፎርም ስራ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች የፈተና ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡
*
መስከረም 29/2018 (አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች እየተሰራ ባለው የሪፎርም ስራ ላይ በዛሬው ዕለት ለተፈታኝ አጠቃላይ ሰራተኞች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
መድረኩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ቢሮው ለሪፎርም በተዘጋጀው ፈተና ዙሪያ ከሲቪል ሰርቪስ እና ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዝግጅቱ አልቆ የፈተና ቀን መወሰኑን በመግለፅ፤ በፈተናው እና በሚደረግ የሰራተኞች ድልድል ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ብርሃኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ በበኩላቸው ማወቅ ለፈተና ብቻ ሳይሆን ለህይወታችንም አስፈላጊ በመሆኑ ለፈተናው መዘጋጀት እንጂ መጨናነቅ እንደማያስፈልግ ገልፀው አጠቃላይ ስለ ሪፎርም ሂደቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርሲቲ ተገኝተው አጠቃላይ የፈተናውን ሂደት ማብራሪያ የሰጡት ዶክተር መሳይ እና ኮማንደር ሲሳይ ሲሆኑ የፈተናው ሁኔታ ላይ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ መሆኑን ገልፀው ፈተናውን ለመፈተን ወደመፈተኛ ማዕከል የሚገባ የትኛውም ሰራተኛ ማማላት ስለሚገባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች ገለፃ ተደርጓል፤ ሰራተኛው በያዘው መደብ ላይ ብቃትና እውቀት ሊኖረው እንደሚገባም ተገልጿል፡፡