ቢሮዉ የነባር የቅጥር ጥበቃ አባላት 1ኛ ኮርስ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮዉ የነባር የቅጥር ጥበቃ አባላት 1ኛ ኮርስ ከምልመላ እስከ ምረቃ የነበረውን ሂደት ገመገመ። ***

ቢሮዉ የነባር የቅጥር ጥበቃ አባላት 1ኛ ኮርስ ከምልመላ እስከ ምረቃ የነበረውን ሂደት ገመገመ።

***

ጥቅምት 01/2018(አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ነባር የቅጥር ጥበቃ አባላትን በ1ኛ ኮርስ በንድፈ ሀሳብና በወታደራዊ የመስክ ስልጠና በማሰልጠን በአካልና በአመለካከት በማብቃት በደማቅ ስነ-ስርዓት ማስመረቁ ይታወሳል።

በዛሬዉ እለትም ከምልመላ እስከ ምረቃ የነበረውን ሂደት የ11ዱ ክፍለ ከተማና የ113ቱ የወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች እና የአዲስአበባ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት አመራሮችና አባላት በተገኙበት ሂደቱን ገምግሟል።

መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/የቢሮ ሀላፊና የዘርፉ ሃላፊ ሲሆኑ፤ወጥ ያልነበረውን የቅጥር ጥበቃ ስምሪት፣ አለባበስ አመለካከታቸው ወደ አንድ ማምጣት መቻሉን ገልፀው፤ የአየር ሁኔታ ሳይገድባችውና ሳትሰላቹ ለተከታይ ለ12 ቀናት የንድፈ ሀሳብ እና የወታደራዊ ስልጠና አሰልጥናችሁ ለመስቀል ደመራ እና ለእሬቻ በዓላት በሰላም ተከብሮ ለማለፉ ስንቅ የሆኑትን የሰላም አምባሳደሮች በማብቃታችሁ ልትመሠገኑ ይገባል በማለት ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

አቶ ሚደክሳ በሰላም ግንባታ ሂደት ዉስጥ የቅጥር ጥበቃ አባላት አደረጃጀት ትልቅ እገዛ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ስልጠናው ቀጣይነት እንደለው በማዉሳት፤ትልቁ አቅምና የሎጅስቲክ ምንጭ ህዝብ መሆኑን እና አዲስ አበባ ከተማ ከሌሎች ክልሎች የተሻለ ሰላም ለመሆኗ አንዱ ምክንያት የፀጥታ መዋቀሮችና ህዝቡ ተቀናጅተው በመስራታቸው ነውና፤እነዚህ ዝ አደረጃጀቶች ትልቅ አቅም መሆናቸውን ተረድተን ትክክለኛ ስምሪት መስጠት ይገባል ብለዋል።

የቦሌ ክ/ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት አስተባባሪ የሆኑት ኮማንደር አጀመ ቤጊ በበኩላቸው ፤የቅጥር ጥበቃ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆናቸው ይህ ሃይል በበዛ ቁጥር የህዝቡ የሰላም ባለቤትነት እንደሚጨምር ጠቅሰው ከተማችን አዲስ አበባ ለማድረግ ለቱሪስቶች እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጠላቶቿ ደግሞ ህመም እንድሆን ለማድረግ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ ስራችን አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል።

መጨረሻም የዘርፉ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ልቅናው ታሪኩ የስልጠናው የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤አቶ ሚደክሳ እና ኮማንደር አጀመ ማጠቃለያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።