ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ )

*

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ከሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ዳይሬክቶሬቶች ጋር ግምገማ አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተናገሩት የ2018 በጀት ዓመት በከተማው ላይ የተከበሩ የሃይማኖትና ህዝባዊ በዓላት ኩነቶች ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ የተጠናቀቀበትና ለሌሎች ስራዎቻችን በተምሳሌነትና ተሞክሮ የሚወሰድ እንዲሁም በቀጣይ በከተማችን የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የማህበረሰብና የፀጥታ መዋቅርን በማቀናጀት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ትላልቅ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ መስጠት አለብን ብለዋል።

ሀላፊዋ አክለውም ከወንጀል መከላከልና መቀነስ ስራዎቻችን ጋር ተያይዞ እጅግ ውጤታማ የሆነ ስራዎች መሰራታቸው፣የደንብ ማስከበር በደንብ መተላለፍ ጥሰቶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስጠታቸውንና የተወሰዱ እርምጃዎች አስተማሪና የምንሰራው ስራ አሁንም ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በተለይም የተቋማት ግንባታ፣በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎትን ማሳለጥ ማህበረሰቡ እየሰጠ ያለው አስተያየት ምንድነው የሚለውን በማየትና ተቋማችን ከብልሹ አሰራርና ሌብነት የፀዳ አሰራር እየሰራ እንደሆነና ተቋሙ ያለበት ደረጃ መከታተልና ማየት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

በግምገማውም ላይ የሁለቱም ተቋማት የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳሬክቶሬቶች የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም ወቅት፣በተቋማት የስራ አመራር ስርዓት ውጤታማነት ማሻሻል፣የማህበረሰብና የፀጥታ ስራዎችና የአደረጃጀት ምልመላ፣ግንባታና ስምሪት ተግባራዊ ማድረግና የማህበረሰብ ተሳትፎ ማጎልበት፣የፀጥታ መረጃዎች ጥቆማ መቀበል፣ማጣራት፣መተንተን እና ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ፣ወንጀል መከላከል፣የፀጥታ ኦፕሬሽን ስራዎች የግጭት አፈታትና፣ከኢኮኖሚ አሻጥር ጋር ተያይዞ ከሌሎች ሴክተርች ጋር በመቀናጀት ክትትል ማድረግና እርምጃ የመውሰድ ስራ፣በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት፣የአገልግሎት አሰጣጥ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች በቅሬታና በአቤቱታ ምላሽ መስጠት፣የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራትን የመከታተል የመቆጣጠርና እርምጃ የመወስድ ስራ በሪፖርቱ አብራርተዋል።

በመጨረሻም በስራ አፈጻጸም ግምገማው ላይ የተሳተፉ አመራሮችና ዳይሬክተሬቶች በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ የሆነ ውይይት ተደርጓል።

በስራ አፈጻጸም ግምገማው ላይ የቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የደንብ ማስበር ባለስልጣን ስራስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ም/ቢሮ ኃላፊዎችና ስራስኪያጆች፣አማካሪዎችና ዳይሬክተሬቶች ተገኝተዋል።