የ2018ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም
ባለፉት ወራት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ አመርቂ ውጤት ከማስመዝገብ በተጨማሪ ከተማዋ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን የማድረግ ስራ መስራት ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
ጥቅምት 6/2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የተጠሪ ተቋሙ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቢሮ የ2018ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በጋራ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በመገምገም ላይ ይገኛሉ ።
በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንደተናገሩት በተያዘው በጀት አመት መግቢያ ላይ ከአገልግሎት ፈላጊው መላው የከተማችን ማህበረሰብ ጋር በመወያየት ወደ ትግበራ ተገብቷል ብለዋል።
ቢሮው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው ከመላው አመራሮች፣ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ ከጸጥታው መዋቅር እንዲሁም ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በተጨማሪም በየደረጃው ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር በመሆን ትላልቅ የአደባባይ በዓላቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው ከመከበሩም አልፎ ከተማውን የቱሪስት መስህብ ከማድረግ በተጨማሪ ያላንዳች ኮሽታ የሀገር ከፍታ ለአለም አመላክተን የህዳሴ ግድብ ያስመረቅንበት ሁሉም የተከበሩት በዓላት በሙሉ በአስተማማኝ ሁኔታ ካለ ምንም የፀጥታ መደፍረስ በዓላቶቹ ከተማውን በሚመጥን መልኩ በሰላም የተከበሩበት እንደሆነም አንስተዋል።
ሀላፊዋ አያይዘውም ከሀይማኖት ተቋማት ጋር እና ከጸጥታው መዋቅር ጋር በተሰራው ስራና በተደረገ ጥረት ለከተማው ተጨማሪ ድምቀት በመስጠትና በዓላት ለማክበር ወደ ከተማው የገቡ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰላም መተው በሰላም ወደመጡበት እንዲመለሱም የማድረግ ስራዎች ማከናወን እንደተቻለም አስታውሰዋል።
በተጨማሪም የጸጥታው አጠባበቅን አስተማማኝ ለማድረግ የሰላም ሰራዊትንና የቅጥር ጥበቃን እንደ አዲስ በመመልመልና ስልጠና በመስጠት ነባሩን አቀናጅቶ በማሰማራት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት እንዲሆን በየአካባቢው ህብረተሰብ አቀፍ ውይይት በማድረግ በመልካም አስተዳደርና በጸጥታ አጠባበቅ ዙሪያ እንዲወያዩ የወንጀል ምጣኔዎች የጸጉረ ልውጥ የሽብር ሀይል ሴራን የማክሸፍና በየአካባቢው የነበሩ ለወጣቶች አልባሌ ቦታ እንዲዉሉ ሲያደርጉ የነበሩ የቁማር ቤቶችን የማጥፋት በየቦታው የሚስተዋሉ ወንጀል የሚፈፀምባቸውን ቦታዎች የመለየትና የመቀነስ የመከላከል ስራ በሰፊው ከመሰራቱም በተጨማሪም የመሬት ወረራና ግንባታ ቁጥጥር በማድረግ ላይ የነበሩ ስርአቶችን ህግ የማስያዝ ወደ መስመር እንዲገቡ የማድረግ ስራ መከናወኑን አንስተዋል ።
በግምገማዊ ውይይት መድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ የሁለቱም ተቋማት ም/ቢሮ ሀላፊዎች አማካሪዎች፣የጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የሁለቱም ተቋማት የሁሉም ክ/ከተማና ወረዳ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።