በሃገር በቀል የሰላምና መቻል ዕሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ
ኢትዮጵያ እና ከተማችን አዲስ አበባ አሁን ያለችበት በእምርታ የማንሰራራት ምዕራፍ ላይ የሴቶች ሚና አይተኬ ነው"።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
***
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በሃገር በቀል የሰላምና መቻል ዕሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ እና ከሴቶች የሚጠበቅ ሚናን አስመልካች ከከተማው ሴቶች ጋር ከተማ-አቀፍ ኮንፈረንስ አካሄደ።
የእለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት አሁን ያለንበት ምዕራፍ ኢትዮጵያና ከተማችን አዲስ አበባ በእምርት እያንሰራራን ያለንበት ወቅት ነው በዚህም የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን ገልፀዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አክለውም የጽናት የህብረትና የትጋት ውጤት የሆነው ህዳሴ ግድባችን አስመርቀን ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነበትና፣ከተማችንም ሁለተናዊ በሆነ መልኩ በኮሪደር ልማት እንደ ስሟ አበባና አዲስ ሆና እየተሰራች እንደምትገኝም በንግግራቸው ገልጸዋል።
ሀላፊዋ አክለውም በነዚህ ትላልቅ ውጤቶች ላይ የሴቶች መሪነት ሚና ጉል መሆኑን ገልጸው፣የሀገራችን ድህነትና የኃላቀርነት ታሪክ የሚቀይሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መሰራታቸው የታሪኩ ባለቤት በመሆናችን አሁንም ሰላማችንን አደጋ ላይ ለመጣል ሌት ተቀን አቅደው የሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች በመከታተል የተለየ የጸጥታ ችግሮች ሲኖሩ ለፀጥታ ሀይሉ መረጃ ቶሎ በመስጠት አከባቢያቸውንና ከተማውን መጠበቅ አለባቹ ሲሉ አንስተዋል።
ሰላም የሁሉም መሰረት እንደሆነና ሴቶች የሀገርና የህዝብ አንድነት መሰረት የሆኑ የአብሮነት ገመዶች እንዲጠናከሩ እየተሰራ እንደሆነና አህጉራዊ፣ሀገራዊና ከተማዊ ጉባኤዎችንና ኮንፈረንሶች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያልፍ ጉልህ ሚና ማድረጋቸውንም አብራርተዋል።
አቶ ብርሃኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሃይማኖትና ሰላም እሴት ዘርፍ ኃላፊ የዛሬው መድረክ በሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል ዕሴት ለትውልድ ግንባታ ያለውን ፋይዳና ተያያዥ ጉዳዮች በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የከተማን ሁኔታን የመቃኘትና ቀጣይ ከሴቶች የሚጠበቀውን ሚና ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነም ጠቁመዋል።
አቶ ብርሃኑ ረታ አክለውም ከተማችን አዲስ አበባ የብዙኃነት ማዕከል፣በአንድነት የተጋመዱ ህዝቦች ያሏትና መሰረት ጽኑ፣የመላ ኢትዮጵያዊ አፍሪካዊያን ብሎም አለም አቀፍ ተቋማት መገኛ እንደመሆኗ መጠን፣ነዋሪዎቿ የብሔርና የእምነት ማንነት ሳይገድባቸው ተዋደው፣ተባብረው ተቻችለው የሚኖሩባትና በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው ከተሞች መሀል አንዷ ስትሆን ከተማችን በሁሉም መስክ አጅግ አስደናቂ ውጤት ያመጣችበት አንዱ ሚስጥር በአንድ እጅ ልማትና በሌለኛው ደግሞ ሰላምን ማዕከል በማድረግ መስራት በመቻሏ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የዛሬው መድረክ በሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል ዕሴት ለትውልድ ግንባታ ያለውን ፋይዳና ተያያዥ ጉዳዮች በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የከተማን ሁኔታን የመቃኘትና ቀጣይ ከሴቶች የሚጠበቀውን ሚና ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነም አቶ ብርሃኑ ጠቁመዋል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሴት አደረጃጀት አማካሪ ወ/ሮ የሺ ወልዴ፣በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ፣ እንዲሁም ከአስራአንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ሴት አደረጃጀቶች ተገኝተዋል።