የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ201...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት አመት የ1ኛሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።

የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት አመት የ1ኛሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።

ጥቅምት 19/2018

***

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጻም ግምገማ አካሄደ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ሲሆኑ፤ የ1ሩብ አመት የተመዘገበው አፈጻጸም ጥሩ እንደሆነ ጠቅሰው በማመስገን፣ ትልቁ የኛ ስራ የሰው ልብና አይምሮ ላይ መስራት ነውና በሰዎች ህሊና ውስጥ ሰላምን በመገንባት በሂደት ወንጀልን ከመቀነስ አልፎ እንዲጠፋ ለማድረግ በርትተን መስራት አለብን ብለዋል። ሰላም ለማጽናት የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የተረጋጋ ፖለቲካና የማህበረሰባዊ ፍትህ እንደሚያስፈልግ በመግለፅ፣ ማንም ሰው ላለበት ቦታ ጥሩ አሻራ አስቀምጦ ማለፍ አለበትና ሁላችንም ተጋግዘንና ተደጋግፈን ያለምንም መሰላቸት ህዝቡን በማሳተፍ የከተማዋን ሰላም መረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል ።

የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉቀን እንየው የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ባቀረቡት ወቅት፤ በሩብ አመቱ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ ጠንካራ ጎኖች እና የነበሩ ክፍተቶችን ገልጸው፣ የበጎ ፍቃድ ወጣቶችን የማሰማራትና የመደገፍ ስራዎች፣ የሰላም እሴትን በመገንባት ህዝቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ ኮንፈረንስ ማካሄዱ፣ ስልጠና መሰጠቱ፣ "ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት" በሚል ሪዕሰ ጉደይ ፓናል ውይይት መካሄዱን እና ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክብረ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲጠናቀቁ ለማድረግ የተደረገ ቅድመ ዝግጅትና የሃይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው አካላት ጋር ቀደም ብሎ ማወያየት መቻሉ እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት ሰላምና ልማት ላይ ተሳትፏቸውን ማሳደግ መቻሉን አብራርተዋል።

በመጨረሻም የቀረበው ሪፖርት ላይ በታዳሚዎች ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቶ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታን ጨምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በቀጣይም በሰላም ግንባታ ላይ ስልጠና መስጠት፣ ካንፍረንሶችና ፓናል ውይይቶች መካሄድ፣ በትምህርት ቤቶች የሰላም ክበባትና የተመሳሰሉትን ማወያየት፣ አገር በቀል እሴቶችን የሰላም እሴቶች እንዲተገብሩ የማድረግ ስራ በስፋት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።