የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም ዋና ዋና ስራዎችንና የቀጣይ የሶስት ወራት የስራ የትኩረት አቅጣጫ ስራዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም ዋና ዋና ስራዎችንና የቀጣይ የሶስት ወራት የስራ የትኩረት አቅጣጫ ስራዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
ጥቅምት 20/2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ የዘርፉ አጠቃላይ ባለሙያዎች ጋር በ2018 ዓ.ም ዋና ዋና ስራዎችና የቀጣይ የሶስት ወራት የስራ የትኩረት አቅጣጫ ላይ በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መድረኩን በመሩበት ወቅት እንዳሉት በተደጋጋሚ በከተማው አስተዳደር ዕውቅናን አግኝቶ ተሸላሚ ወደ ሆነው ቢሮና ጠንካራ አመራሮች እና ሰራተኞች ወዳሉበት ተቋም በመምጣቴ ደስታ ይሰማኛል በማለት
ሰላምን በጋራ ለማረጋገጥ የሁላችን ሀላፊነት እንደመሆኑ መጠን የሚሰጡ ስራዎችን በጥራትና በተቀላጠፈ መልኩ በሚገባ በመስራት የላቀ ውጤት በቀጣይም ማስመዝገብ ይገባል ያሉት ሀላፊው አዲስ አበባ 7/24 የምትተጋ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ህብረተሰቡ በተፈለገው ልክ ግልጋሎት አግኝት ተንቀሳቅሶ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ የማድረግ ስራ በማከናወን ከጸጥታ አንጻር ከተማውን የሚመጥን ደረጃውን የጠበቀ የጸጥታ ስራ ማከናወን ይገባልም ብለዋል
ኃላፊው አክለውም የጠላት ሀይል ሴሎች እንዳሰቡት መንቀሳቀስ ያልቻሉት በከተማው ውስጥ የተደራጀውና ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው የሰላም ሰራዊቱ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ እሱን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ህብረተቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና ለውጥ የሚያመጣ የህብረተሰቡ ተኮር ውይይቶችን በማጎልበት ወንጀለኞች ወንጀል ፈጽመው የሚሸሸጉበት ሳይሆን ማምለጥ የማይቻልበት ከተማ በማድረግ ወንጀልን የሚጸየፍ ትውልድ በማነጽ ተቻችሎ ተከባብሮ አንድነትን የሚሰብክ ማህበረሰብ በመፍጠር ከተማው አሁን ካለበት ቁመና የበለጠ ሰላም የሰፈነበት የማድረግ ስራ ይጠበቅብናልም ሲሉ ተደምጠዋል።
የዘርፉን ዋና ዋና ስራዎችን በተመለከተ አቶ ልቅናው ታሪኩ የዘርፉ ቡድን መሪ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ስለ መረጃ ማጣራት፣ስለ ዘርፍ አደረጃጀቶች፣ስለ ግጭት አፈታት፣ስለ ማህበረሰብ ምክክርና ውይይት፣ስለ ስጋት ቦታዎች መለየት ዋና ዎቹ መሆናቸውን አመላክተዋ።
አጠቃላይ ከሰራተኞቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ከሀላፊው ምላሽ በመስጠትና በቀጣይ በሚሰሩሩ ስራዎች ላይ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
በመድረኩ ላይ አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።