ሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸዉ ፋይዳ እና የወጣቶችን ሚና አስመልክቶ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
ሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸዉ ፋይዳ እና የወጣቶችን ሚና አስመልክቶ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
***
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ጋር በመቀናጀት ሀገር፥ በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትዉልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ እና የወጣቶችን ሚናን አስመልክቶ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ አካሄዱ።
ኮንፈረንሱ በተካሄደበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ሲሆኑ በንግግራቸውም ወቅትም የዛሬው መድረክ ሃገር በቀል የሰላም መቻቻል ዕሴት ለትውልድ ግንባታ ያለውን ፋይዳና ተያያዠ ጉዳዮች በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ከወጣቶች የሚጠበቀውን ሚና ታሳቢ በማድረግ እና ሀገራዊ አንድነትን እና ውህደትን ለማሳደግ፣የሀገር ፍቅርን፣ሰላማዊ አብሮ መኖር እና ማህበራዊ ትስስር ለማጎልበት ወጣቶች በሀገራቸው ሰላምና ልማት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ፣በብቃት ጎልብተው ለማህበረሰባቸው አባላት ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዲሆኑ የሁሉ መሠረት በሆነው ሰላም ላይ መነጋገር እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ ነው ብለዋል።
በከተማችን ብዙ ወጣቶች የሰላም አባሳደር በጎ ፈቃደኞች ሆነው ያገለግላሉ ያሉት አቶ ብርሃኑ ረታ፣ያለመታከትም እየሰሩ እንደሆነና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የበለጠ ሰላማዊ እና ጠንካራ ማህበረሰቦችን ለመፍጠርም የከተማችን ወጣቶች ተምሳሌታዊ ስራ መጀመራቸውን፣የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምረቃን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ ቲክቶከሮች ያደረጉት ርብርብ እንዲሁም ወጣቶች በሀገር በቀል የሰላም ዕሴቶች እንዲሰሩ በማድረግ ሀገርን መገንባት አለባቸው ሲሉም ተደምጧል።
በኮንፈረንሱ ላይ በሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል ዕሴቶችን ለትውልድ ግንባታ ስላላቸው ፋይዳ በተመለከተ መነሻ ጹሁፍና ጥናታዊ ምርምር ያቀረቡት ዶክተር ታምሩ ፈይሳ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ ሲሆኑ፣መነሻ ጹሁፉንና ምርምሩን ባቀረቡበት ወቅት የሰላም መቻቻል ባለበት ሀገር ውስጥ ሰላም ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ እንደሆነና በትውልድ ቅብብሎሽ አንድ የሆነች ሀገር እንደሆነችም ጠቅሰው፣ሀገር በቀል ዕሴቶችን የጋራ መሆናቸውን በመረዳት ለትውልዱ በማስተላለፍ የሀገር ማንነት ጠብቆ የወጣቶች ሚና የጎላ በመሆኑ የመቻቻል፣የአብሮነት እሳቤ በማስተላለፍ ሰላምን ማስቀጠል እንደሚገባ በሰነዱ አብራርተዋል።
ከተማችን ላይ አስተማማኝ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በከተማችን፣በአከባቢያችን ባህላዊ የግጭት አፈታት፣በርካታ የሀገራችን ዕሴቶችን ወጣቱ አጠናክሮ ለትውልዱ በማስተላለፍ ለሰላም ግንባታ፣የልማት ስራ የመልካም አስተዳደር ስራ ላይ ተሳትፎዎቻቹን በማድረግ ውይይታቹን በማዳበር የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን ለፀጥታ አካላት በመስጠት ሚናቹን መወጣት አለባቹ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣት ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ በረከት ቢርቢሳ ተናግረዋል።
በመድረኩም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣት ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ በረከት ቢርቢሳ፣በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ፣ ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ወጣት ማህበር ተገኝተዋል።