የሰላም እሴትና መቻቻል ለሃገርና ትውልድ ግንባታ ያለው ፋይዳ በሚል በከተማ እና በክ/ከተማ ደረጃ ሲደረግ የነበረው ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መርሐ ግብር
የሰላም እሴትና መቻቻል ለሃገርና ትውልድ ግንባታ ያለው ፋይዳ በሚል በከተማ እና በክ/ከተማ ደረጃ ሲደረግ የነበረው ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
ህዳር 4/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴትና መቻቻል ለሀገር ትውልድ ግንባታ ያለው ፋይዳ በሚል ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በማካሄድ ላይ ነው ።
በኮንፈረንሱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ኢትዮጵያዊያን አንድ ቦታ ብቻ ስንገኝ ብቻ አንድ መሆን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ቦታ መከባበርንና መቻቻልን በየትኛውም ቦታ በመስበክ ስለ ሰላም ብዙ ተብሎ አሁን ላይ ላለንበት ለውጥ እደሰናል በማለት አንድነት በማጠናከር የአንድ እናት ልጆች ስለሆንን ልዩነቶች ሳይፈጠሩ በየቤተ እምነታችንና በየ ማንነታችን አንድነትን በመፍጠር ቀድሞ የነበረንን ነገር በተዋረድ ማስቀጠል እንደሚገባ ሀላፊው አሳስበው
በተፈጥሮ ልዩነቶች ቢኖሩም ልዩነቶችን ትተን አንድ በመሆንና የሰላም አምባሳደር ለራሳችን በመሆን መቻቻልን በመስበክ ለትውልድ በማስተማር እኔነትን ትተን የእኛነትን መንፈስ መግባባቶችን መፍጠር ይገባል ሲሉ የተደመጡ ሲሆን
የጎደለን ነገር ስለሌለ ያለንን ንጹህ ሀብት በጋራ በመጠበቅና በመጠቀም ኢትዮጵያን መገንባት በተለይ ደግም ከለውጡ በሏላ የተሻለ አስተሳሰብ ህብረተሰቡ ውስጥ ስላለ ለትውልድ የምናስተላልፈው የምንናገረው የጋራ ታሪክ ማስቀመጥ መልካም ፍሬን ጠብቆ ማስቀመጥ የሁላችንም ድርሻ መሆን ይገባናል ሲሉ ተደምጠዋል ።
አቶ ብርሀጉ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎቿ ተባብረውና ተቻችለው አንድ በመሆን የሚኖሩባት በመተባበር አቅፍና ደግፋ በመያዝ ሁሉም የእጅ ስራውን ያሳረፈባት የአፍሪካውያንና የአለም አቀፍ ተቋማት መሰብሰቢያ ትልቅ ከተማና በፈጣን የእድገት ደረጃ ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ ናት በማለት የተደመጡ ሲሆን
ከተማዋም በሁሉም መስክ እጅግ አስደናቂ ውጤት ያመጣችበት ዋናውና አንዱ ሚስጥር በአንድ እጅ ልማትን ደግሞ በሌላው ሰላምን ማዕከል በማድረግ ሁሉንም በየደረጃው በማሳተፍ በባለቤትነት ስሜት እንዲሰራ ማድረግ በመቻሉ የመጣ ውጤትም እንደሆነ ገልጸው ስለ ሰላም እሴት ግንባታ መነጋገር የተፈለገበት መንገድ ሰላምን በማስረጽና የሚያጋጥሙ ግጭቶች እንዳይባባሱ በማድረግ በኩል ሀገር በቀር እሴቶችና ባህላዊ ትውፊቶቻችንን ለውውይይትና ምክክር ለትምህርትና ግንዛቤ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ በተቃርኖ የሚታይ የሚመስሉንን እሳቤዎች እንድ ላይ እንዲቀራረቡ የሚያደርግ ሀይል አላቸውም ሱሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።
ሀላፊው አያይዘውም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የጋራ ስምምነትና መግባባትን የሚፈጥሩ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሌሎችም አውዶችን መገንባት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ዋናውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ተግባር ዘላቂ ሰላምን ከማምጣት ጋር ተያይዞ በመሆኑ ከአሉታዊ ሰላም የሚመጣው እሳቤ በመቀልበስ በሰዎች መካከል ያለውን ተግባቦትና ስምምነት በማራመድ አንድ ወደ ሚያደርገን ሰላም ላይ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ በአደራ ጭምር ተናግረዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ፣አቶ ብርሀኑ ረታ የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ፣ክቡር ዶክተር ታምሩ ፈይሳ የሀይማኖት አባቶች ፣አባ ገዳዎች፣ሃደ ሲንቄዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።