ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስል...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

የከተማቸውንና የአከባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የአካል ጉዳተኞች ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለጸ።

ህዳር 5/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶችና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በጋራ በመተባበር ከሃይማኖትና የሰላም ግንባታ ዘርፍ "በሀገርና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ ሀገራዊ-ማንነት መገንባት" በሚል ርዕስ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በሰላም ጉዳይ ህዝባችንን በማካተትና የሰላም ባለቤት በማድረግ የጋራ ስምምነትና መግባባትን የሚፈጥሩ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሌሎችም አውዶችን በመገንባት ዋናውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ዘላቂ ሰላምን ማምጣትና ብልጽግናችን እውን ይሆን ዘንድ በሁሉ መስክ ማሳተፍና ባለቤትነትን የማረጋገጥ በሚል የሚሰራ ነው ብለዋል።

በከተማችን የሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ማህበር የፅናት የብርታት የአርያ ተምሳሌት ናቹ፣ያሉት አቶ ብርሀኑ ይህ የአካል ጉዳተኛ ማህበር በየአከባቢያቸው በሰላም ሰራዊት በመደራጀት መረጃዎችን በመስጠት የአከባብያቸውንና የከተማዋን ብሎም የሀገር ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የበኩላቸውን ሚና ተወጥቷል ሲሉ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ገነት ቅጣው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ም/ል ቢሮ ኃላፊ የዛሬው መድረክ አካታችነት የሀገር ብልጽግና አካል ጉዳተኞች ማረጋገጥ ሲሆን፣ሰላምን መጠበቅ ማረጋገጥ አካል ጉዳተኞች በሰፊ ወጥቶ፣በኢኮኖሚ በፖለቲካ ማሳተፍ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አካታችነትን በተግባር ያሳየና የብልጽግና ሁለተናዊ ተሳታፊነቱን የሚረጋገጠው የአካል ጉዳተኞችን በማሳተፍ ያለምንም ስጋት ወጥቶ እንዲገባ በሰላምና በፀጥታ ጉዳይ ላይ በማወያየትና በመነጋገር ችግሮችን እንዲፈቱ የታለመ የግንዛቤ መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከሃይማኖትና የሰላም ግንባታ ዘርፍ "በሀገርና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ ሀገራዊ-ማንነት መገንባት" በሚል ርዕስ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን፣ሰነዱን ያቀረቡልን የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ከፍተኛ የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ኤልያስ ቀጀላ"በሀገርና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ ሀገራዊ-ማንነት መገንባት" በሚል ርዕስ ላይ የሚዳስስ ሰነድ አቅርበዋል።

አቶ ኤልያስ አክለውም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ የጋራ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ነው ብለዋል።

ሁለተናዊ ብልጽግና እንዲመጣ የጠላት መሳርያ ሳትሆኑ፣ መረጃ በመስጠት የከተማዋንና የአከባቢያቹን ሰላም በማስጠበቅ የበኩላቹን ሚና እንድትወጡ ሲሉ አቶ ብርሃኑ በማጠቃለያቸውም ጰመልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶችና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳዮች ም/ል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣቱ፣የማዕከልና የክ/ከተሞች የዘርፉ ዳይሬክተሬቶች፣አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎች እና ከ11ዱም ክ/ከተማ የተወጣጡ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ተገኝተዋል።