የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማዕከል ባለሙያዎች የክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር የዘርፉን ስራዎች በጋራ ገምግመዋል።ገምግመዋል።
የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማዕከል ባለሙያዎች የክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር የዘርፉን ስራዎች በጋራ ገምግመዋል።
ህዳር 9/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ. ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማዕከል ባለሙያዎች ከ/ክ ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር በጋራ ስራዎችን ገምግመዋል።
በስራዎቻቸው ላይ ስለሚከናወኑት ተግባራት በጥንካሬ በድክመት በቀጣይም ስለሚከናወኑት ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉት አቶ ልቅናው ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አጀረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ በቀረበው ገለፃ ላይ ተመርኩዘው ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱን የመሩት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ ህብረተሰቡን ከምንግዜውም በበለጠ መልኩ በማሳተፍ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት በማድረግ የተፈቱ ችግሮችን በመለየት አዳዲስ ግኝቶችን በመለየት የሰላም ሰራዊቱን በአቋም በባህርይ የተሻለ አቋም እንዲኖረው በማድረግ በሶስት ሺፍት እንዲሰሩ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ማስኬድ ይገባል በማለት
የሚሰሩ ስራዎችን በደንብ አድብቶ በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባና ተልዕኮውን የሚወጣ ተግባራዊ የሚፈጽም የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ማስቀጠል ጭምር አስፈላጊ ስለሆነ በቁርጠኝነት ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል ።
ሀላፊው አያይዘውም በአዳዲስ ፈጠራዎች በመታጀብ ክህሎችን በማሳደግ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅና በማረጋገጥ ከተማውን ሰላም የሰፈነበት በማድረግ መንግስት የሰጠንን ሀላፊነት በተገቢው መንገድ በመወጣት በቀጣይ ከአደጋዎች በፊት አደጋ የሚያደርሱ ድርጊቶችን በመለየት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ነባሩን የሰላም ሰራዊት አባላትን በማጠናከር የስጋት ቦታዎችን በመለየት አደረጃጀቶች ላይ ይበልጥ በመስራትና የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅ የሁላችን ድርሻ መሆን ይገባዋል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።