በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።
በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።
ህዳር 23/2018 ዓ.ም(ሰፀአስ ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት አድርጎ እየሰራ የሚገኘ ሲሆን የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚነኙ ማህበረሰብ ተኮር አመቻችቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፍት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አጀረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት ቢሮው ባለፍት አመታት ውስጥ ማህበረሰቡን በየአካባቢው በተለያየ ርዕሰ ጉዳይና ያለመግባባት ላይ በመመካከር የውይይት ባህልን በማዳበር እረገድ በየግዜው ግለሰቦች በሚኖሩበት አካባቢ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስታውሰው
ግለሰቦች ችግሮቻቸውን በውይይት በመነጋገር በይቅርታ እንዲፈቱ ከማድረግም ባሻገር የሀገር ባህልን በርካታ እሴቶችን ይዞ የመጣ የአባገዳ ስርአት በየቤተእምነቱ የእርቅ ስነ ስረዓት እንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ ተሰሚነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶችን በመፍታት የመጣን ህዝብ በሸንጎ በእርቅ በመፍታት ወደ ከረረ ነገር እንዳይገባ በማድረግ ቁጭ ብለው ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ አመቻችቶ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ምስጋናን በማቅረብ
በየግዜው የሚደረጉ ውይይቶች ጠቀሜታቸው እጅግ የጎላ ነው ያሉት ሀላፊው አለመግባባቶችን በድግግሞሽ በውይይቶች መነጋገር ጥቅሙ ሰላም እንዲሰፍን እርስ በርስ መደጋገፍ መግባባት ተሰሚነት እንዲኖር የጋራ አቋም በመያዝ ማህበረሰቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን በሰላም ጉዳይ ባለቤት እንዲሆን ማብራት የማብራት ስራን አጠናክረው ማስቀጠልና በሰላም ጉዳይ ላይ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች ላይ በሙሉ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስልጠናው የሰጡት አቶ ልቅናው ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ ስለ አመቻችነት፣ስለ አርያነት፣ስለ መሪነት፣ስለዳኝነት፣ሰላምን ስለመገንባት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከገለጻው በሏላ ከአመቻቶቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
በዛሬው የአመቻቾች ተወካዮች ስልጠናው የወሰዱት ክ/ከተሞች ን/ላፍቶ፣ቦሌና አቃቂ ካሊቲ የተካተቱ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ክ/ከተሞች ስልጠናውን እንደሚወስዱ ለማወቅ ተችሏል።