የቀጠለ ዜና
በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች እየተሰጠ የሚገኝው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ።
ህዳር 24/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ባለቤት አድርጎ እየሰራ የሚገኘ ሲሆን የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚነኙ ማህበረሰብ ተኮር አመቻችቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ቀጥሎ ውሏል ።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፍት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አጀረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት ቢሮው ባለፍት አመታት ውስጥ ማህበረሰቡን በየአካባቢው በተለያየ ርዕሰ ጉዳይና ያለመግባባት ላይ በመመካከር የውይይት ባህልን በማዳበር እረገድ በየግዜው ግለሰቦች በሚኖሩበት አካባቢ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅሰው
በየአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በተፈጥሮ ኢደት የሚፈጠሩ ያለመግባባት ችግሮችን አንድ በመሆንና በመስማማት ኢደት ውስጥ በውይይት በመነጋገር ችግሮቻቸውን በይቅርታ እንዲፈቱ ከማድረግ ባሻገር አሁን ላይ እየጠፋ የሚመስል ነገር ግን ያለና የሚኖር ባህላችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ እሴቶቻችንን ይዞ በማስቀጠል በኩል የበኩላችሁን አስተዋዕኦ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳትሉ የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ በኩል ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባችሏል ሲሉ ገልፀዋል
ውይይቶችን በሀገረ ባህል ፍቅር መሰረት በማድረግ እንድነት እንዲኖር በአካባቢ ጉዳዩች ላይ የራስን ሀሳብ የጋራ አድርጎ በጋራ መግባባት እንዲቻል ችግሮችን የመፍታት ኢደቱ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውና ውይይቶቹ በሙሉ የችግሮቻችን መፍትሔ ሆኖ በማስቀጠልና አለመግባባቶችን በንግግር በማሸነፍ የመነጋገርና የመግባባት ችሎታንም በአንድነት የማዳበር ጥቅሙ የጎላ ከመሆኑ ባሻገር አካባቢን በመጠበቅና ሰላም እንዲሰፍን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በኩል በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበትና ከስልጠናውም በሏላ ለቀሪው ማህበረሰብ አስፈላጊውን መልዕክት በማስተላለፍና በየአካባቢያችን ላይ የሚፈጠሩ ድንገተኛ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሀላፊው አያይዘውም ከተማዋ በፈጣን እድገት ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የብዙ ሰወች አይን የሚያርፍባት ሰላሟም አብሮ የተረጋገጠባት ለኑሮ ምቹ ከተማ እንደመሆኗና ተፈላጊነቷ የጎላ ትላልቅ የህዝብና የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የተደረገው የህብረተሰቡ የምክክር ለውጡ አንዱ ማሳያ ለውጥና ተሳትፊውም በሰላም ጉዳይ ላይ የጎላ ከመሆኑ ጋር ጋር ተያይዞ የመጣው ለውጥ በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰተው ተናግረዋል ።
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ከበደ ለገሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ ስለ አመቻችነት፣ አርያነት፣ መሪነት፣ዳኝነት፣ሰላምን ስለመገንባትና አንድነት ጉዳዮች ላይ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ከማህበረሰብ ተኮር አመቻች ተወካዩች ስልጠናውን መሰረት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊና የዘርፉ ሀላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
በዛሬው የማህበረሰብ ተኮር የአመቻቾች ተወካዮች ስልጠናው የወሰዱት ክ/ከተሞች አዲስ ከተማ ፣የካ፣ኮልፌና አራዳ ክ/ከተሞች የተካተቱ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ክ/ከተሞች ስልጠናውን እንደሚወስዱና ማጠቃለያው እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡