በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ ።

በየአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ ።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ባለቤት አድርጎ እየሰራ የሚገኘ ሲሆን የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚነኙ ማህበረሰብ ተኮር አመቻችቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል ።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፍት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አጀረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ ቢሮው ባለፍት አመታት ውስጥ ማህበረሰቡን በማሳተፍና በማወያየት ከተማው ላይ ብሎም በየአካባቢው በተለያየ ርዕሰ ጉዳት ላይ እርስ በርስ በመወያየት ያለመግባባት አስተሳሰብን ወደ አንድ አይነት አስተሳሰብ በማምጣት በመመካከር የጠፍ የሚመስል ግን ያለ ባህልን በማዳበር እረገድ በየግዜው ግለሰቦች በሚኖሩበት አካባቢ ችግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን የእርስ በርስ የመግባባት ባህልን በማዳበር በኩል ችግሮችም ሲፈጠሩ እንዲፈቱ በማድረግ በኩል ከቢሮው ጎን በመቆም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እየተወጡ ለሚገኙት የማህበረሰብ ተኮር የምክክር አመቻቾች ምስጋናን በማቅረብ

በየአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በርስ በመመካከር በመወያየት በኩል የምንታወቅ እንደመሆናችን መጠን ችግሮቻችንንም በጋራ የምንፈታ ህዝቦች እንደመሆናችን መጠን ያለመግባባት ክስተቶች ሲፈጠሩ እርስ በርስ በመነጋገር ጸብ ቀስቃሽና ሰላምን ከሚያደፈርሱ ድርጊቶች ማራቅ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

ሀላፊው አያይዘውም በማህበረሰብ ተኮር ውይይቶችን በማጎልበት የአካባቢን ብሎም የሀገርን ሰላም ደህንነት በማስጠበቅ ስለ ሰላም ውይይቶችን በየግዜው በመፍጠር ቂም በቀልን በመተው እንድነት እንዲፈጠር እንዲጎለብት በማድረግ በውይይት የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ በማስቀጠል በከተማው ላይ የታየውን ሰላም በቀጣይ በዘላቂነት ማስኬድ አስፈላጊ መሆኑን ሀላፊው ጠቅሰዋል።

በመጨረሻም ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግና ውይይቶችን ማዳበሩ በርካታ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ብሎም በየትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ አዋኪ ድርጊቶች የኢኮኖሚ አሻጥሮች እዚም እዛም የሚታዩ አዋኪ ድርጊቶች ጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴ ቢኖሩም ሌሎች በርካታ ድርጊቶች ለውጥ ማምጣት የተቻለው ቢሮው በፈጠረው የውይይት ጊዜ እየተፈታ ቢሆንም አሁንም ያልተፈቱና ያልተሻገርናቸው ድርጊቶች ላይ ለጋራ ደህንነት ሲባል በጋራ መስራት እንደሚጠበቅ ሀላፊው አሳስበዋል ።

ስልጠናውን የሰጡት አቶ ልቅናው ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ ስለ አመቻችነት፣ አርያነት፣ መሪነት፣ዳኝነት፣ሰላምን ስለመገንባትና ውይይቶችን እንዴት መምራትና ችግሮችን እንዴት መፍታት እንዳለባቸው ጉዳዮች ላይ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ከማህበረሰብ ተኮር አመቻች ተወካዩች ስልጠናውን መሰረት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊና የዘርፉ ሀላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

በስልጠናው ላይ አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ፣አቶ አበራ የልደታ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊና የሰላምና ጽ/ቤት ሀላፊ ተወካይ፣ኮማንደር ተክሌ የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ም/ዳይሬክተር የልደታ የየካ የቂርቆስና የለሚኩራ የማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ አመቻቾች ተገኝተዋል።