የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዘር...

image description
- Recent News   

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዘርፎች የዘጠኝ ወራት እቅዶቻቸውን ገመገሙ፡፡

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዘርፎች ዛሬ የዘጠኝ ወራት እቅዶቻቸውን በተለያዩ መድረኮች ሲገመግሙ ውለዋል ፡፡የቢሮው የህዝብ ደረጃጀት፤ የሰላም እሴት ግንባታና የኃይማኖት ጉዳዮች፤ የፀጥታ ኦፕሬሽን፤ ዘርፎች ናቸው፡፡በመድረኮቹ ላይ የዘጠኝ ወራት ሪፖርት በማቅረብ ጥልቅ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዶባቸው የቀሪ ሶስት ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡በሪፖርቶቹም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከግቦቻቸው አንፃር የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ስኬቶች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች ተዳሰዋል፡፡በተለይም በሶስቱም መድረኮች ሪፖርቶቹ ከተገለፁ ዋና ዋና ስኬቶች መካከል ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ በተሰራው ስራ ታላላቅ የአደባባይ ኩነቶች ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት፤ ዓለማቀፍ ስብሰባዎች የመሳሰሉት ያለምንም የፀጥታ ችግሮች መከበራቸው፤የተለያዩ ፅንፈኛ ኃይሎች እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ የሽብር እንቅስቃሴዎችን ማምከን መቻላችን ተጠቃሽ ሲሆኑ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ደግሞ አጠቃላይ በቢሮው የሰው ኃይል ዕጥረት፤የሠራተኞች ፍልሰት፤ የአደረጃጀትና የግብዓት ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ውይይቶቹን የመሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች አቶ ጌታሁን አበራና አቶ ሚደክሳ ከበደ ሲሆኑ ከተሰብሳቢዎቹ የተነሱ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ ከሰጡ በኃላ በቀሪ ቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ መተግበር አለባቸው ያሉትንም አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል፡፡