የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 9 ወራት በቅንጅት የተሰሩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል፡፡የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቢሮዉ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማጠናከር የፀጥታ መዋቅሩን ከማህበረሠቡ ጋር በማቀናጀትና የሠላም ባለቤት እንዲሆን በማስቻል በፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ የፀረሰላም ሀይሎችን የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን በማጨናገፍና በመቆ ጣጠር ህገ-ወጥ እና አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል እና ህጋዊ እርምጃ በመዉሠድ፣ በማስወሰድ ደረቅ ወንጀሎችን በመቀነስ በቅንጅት የተሳካ ስራ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡ሀላፊዋ አከለዉም ዘላቂ ሠላም በከተማችን እንዲሰፍንና ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ከመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የተደራጀው የሠላም ሠራዊቱን የሠላም ባለቤት በማድረግ የተሠራው ሥራ፣ውጤት ያመጣው በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከባለሙያዉ ጋር በመቀናጀት መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም የተቋማቱን አቅም በአሰራር፣ በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ በማዘመን በተቀናጀ አግባብ እነዚህን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡:የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ የመሬት ወረራን በማስቆም እና የተወረሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ህገወጥ ግንባታና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዉጤት ያስመዘገብነዉ በቅንጅት ስለሰራንና የአመራር ፑል በመጠቀም ወጥነት ያለዉ ግምገማ በመዋቅራችን ዘርግተን ስለሰራን ነዉ ብለዋል፡፡