የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የቢሮ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የቢሮውን የ6ወራት አፈፃፀም ስራዎች ግምገማ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የቢሮውን የ6ወራት አፈፃፀም ስራዎች ግምገማ አደረገ፡፡
        ****
           ጥር 01/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ በእቅድ ላይ የተመሠረቱ በርካታ ስራዎችን 7/24 የሚል መርህን በመከተል በ2018 በጀት አመት ስምንት ግቦችና በርካታ ዝርዝር ተግባራትን የእቅዱ አካል በማድረግ ወደ ተግባር ገብቶ የበጀት አመቱን የመጀመሪያ ግማሽ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ለተገኙ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና ለቢሮዉ አስተዳደር አካላት አቀረበ።

የቢሮዉ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በ2018 በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት የተሠሩ የሰላም ጸጥታና ደህንነት ስራዎችን ሪፖርት በሰነድ መልክ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ያቀረቡ ሲሆን፤ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ የአገልግሎት አሰጣጥና የቅሬታ አፈታት ስርዓት፣ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ላይ፣የጸጥታ ስራዎች የኢኮኖሚ አሻጥርና ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በማንሳት በከተማዉ የወንጀል ምጣኔን ከባለፈዉ አመት ጋር ሲነጻጸር 44.6 በመቶ እንዲቀንስ ማድረግ የተቻለ መሆኑን በሪፖርቱ የቀረበ ሲሆን ባጠቃላይ በስምንት ግቦች ላይ ተመርኩዞ ቢሮዉ የሰራቸዉን ተግባራት ሀላፊዋ በሠነዱ ዳሰዉ በቀጣይ በትኩረት የሚሰሩ ስራዎችንም በትኩረት አቅጣጫ መልክ አዉስተዋል።

የምክርቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በበኩላቸው በቢሮዉ አማካኝነት በሪፎርም፣በአገልግሎት አሰጣጥና ቴክኖሎጂን ከማዘመን አኳያ የተሠሩ ስራዎችን በማበረታታት በአዲስ አበባ ምክር ቤት ለሰላምና ጸጥታ ቢሮዉ በተዘጋጀው የድጋፍና ክትትል ቼክ-ሊስት  መሠረት ጥያቄና አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን፤የቢሮዉ ምክትል የቢሮ ሀላፊዎችና የዘርፍ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን በንግግራቸውም የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በየ ጊዜዉ የሚያደርገዉ ድጋፍና ክትትል ለቢሮዉ የጸጥታ ስራ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ስለሆነ አባላቱን በማመስገን፣በድጋፍና ክትትሉ ወቅት በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።