ቢሮው በስድስት ወራት በመልካም አስተዳደርና በአ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው በስድስት ወራት በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።

ቢሮው በስድስት ወራት በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።

             ጥር 1/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                           **
በከተማው ውስጥ እንደ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚሰጡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ለማዘመንና ህብረተሰቡን በተፈለገው ልክ ለማገልገል የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በተገቢው መንገድ ሀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በስድስት ወራት ውስጥ በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ሲቪክ ማህበራት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እንዳሉት በከተማው ውስጥ በተለይ ደግሞ ተቋሙ የከተማውን ሰላም በማስቀጠልና በማስጠበቅ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት አማካሪው ከቢሮው ጀምሮ መዋቅሩ እስካለበት ወረዳ ድረስ ለህብረተሰቡ አገልግሎትን እየሰጠ እንደሚገኝም ገልፀው እንደ ተቋም የተሰሩ ስራዎችንና ያልተሻገርናቸውን  በቀጣይ በጋራ በመቅረፍ የከተማው ሰላም ማረጋገጥ ይገባልም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ቢሮውም ትልቁና ዋናው ተግባሩ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ከተማዋ ሰላም የሰፈነባት ጸጥታዋ የተረጋገበጣትና ነዋሪው በሰላም ወቶ እንዲገባ የጸጥታ መደፍረስ እንዳይከሰት የቅድመ የመከላከል ስራዎችን በቅንጅትና በጋራ  እየተሰራ ይገኛልም በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።

ሀላፊው አያይዘውም አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለና ከተማውን የሚመጥን ለማድረግ በተደራጀ መልኩ ቢሮው እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመው ህብረተሰቡ ላይ እንግልት እንዳይገጥም ተግባርና ሀላፊነቱን በተገቢው መንገድ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ጭምር ጠቅሰው  በቀጣይም በተቀላጠፈ አግባብነት ባለው መልኩ አገልግሎትን ለመስጠት ቢሮው በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በመጨረሻም ቅሬታ የሚፈጥሩ ችግሮችን በመፍታት ግልጸኝነትን በመፍጠር ለህብረተሰቡ ፍታዊ የሆነ አገልግሎት በሚገባው መንገድ በመስጠት በአብሮትን በቅንነት በታማኝነት በመስራት የከተማውን ሰላም በጋራ ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉት ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ገለጻ ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጎል።

በውይይቱ ላይ አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ፣የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቂዎች፣የጸጥታ አካላት የሲቪል ማህበራት ተወካዩች፣የመማክርት ጉባኤ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።