የቢሮዉ ጠቅላላ ስትራቴጂክ ካውንስል የ2018 በ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሮዉ ጠቅላላ ስትራቴጂክ ካውንስል የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

የቢሮዉ ጠቅላላ ስትራቴጂክ ካውንስል የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

    ጥር 01/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

                  ***
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠሪ ተቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስትራቴጂክ ጠቅላላ ካውንስል  የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በጋራ  ገምግመዋል።

በጠቅላላ ካውንስሉ ላይ የሁለቱም ተቋማት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፤በሪፓርቶቹም በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት የጸጥታ መዋቅሩ በጥምር ሀይል በመገምገምና ጥብቅ ስምሪት በመስጠት እንዲሁም ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ የተሠሩ ስራዎች፣በከተማዉ የተካሄዱ አለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶችና ሴሚናሮች ያለምንም የጸጥታ ስጋት  ዓላማቸዉ ላይ ብቻ  ትኩረት ተደርጎ መሠራቱ፣ በመዲናዋ የተካሄዱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ህዝቡ የሰላም ባለቤት በማድረግ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ በ6 ወራት ዉስጥ የተሠሩ ስራዎች፣ ህገ ወጥ የጎዳና ንግዶችን ለማስቀረት የተኬደ ርቀት፣አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባር፣ ወንጀል ጠል የሆነ ማህበረሰብ እንዲኖር የተሰሩ ስራዎች፣የኮሪደር ልማት ትሩፋቶች ላይ የሚደርሱ ብልሽቶችን መቆጣጠርና  መሠል በከተማዉ ሰላምን አስፍኖ የህግ የበላይነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ አብይና አበይት ተግባራት በተቋማቱ ሪፖርት ላይ በስፋት ተነስቷል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮዉ  ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  መድረኩን በመሩበት ወቅት በቀረቡት ሪፖርቶች ዙሪያ በተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች ዙሪያ ሰፊ  ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ በ2017 የስራ አፈጻጸም ተቋማቱ  በድል ማጠናቀቃቸውን መነሻ በማድረግ የ2018 በጀት አመትን እቅድ በሁሉም ዘርፍ ግቦች ዙሪያ ዉጤት ሊያስመጡ የሚችሉትን እቅዶች ሁለቱም ተቋማት እንደየ ግባቸዉ ስምሪት እንደሰጡ አንስተዉ 24 ሰዓት በመስራት ሰላምና ጸጥታን በማስፈን የደንብ መተላለፎችን የመቆጣጠር ስራ በመስራት በግማሽ አመቱ በሁለቱም ተቋማት አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡ አዉስተዋል። ሻለቃ ዘሪሁን አክለዉም በቀጣይ ስራዎችም ስኬትን ለማስቀጠል ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ
በአደረጃጀት ጥሩ ዉጤት የመጣበት በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል በማለት ቅንጅታዊ ስራም ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊዋ በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰራት ያለባቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን
በሁለቱም ተቋማት ተቋም ግንባታ ስርዓት  የተጀመሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ መደረግ እንዳለበት አንስተዉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት የመስጠት ስራን ማጠናከር ፣በአመለካከትና በስነምግባር የተቀየረ ሌብነትና ብልሹ አሰራር የሚጸየፍ በሚሰራው ስራ ውጤታማ የሆነና ተወዳዳሪና ብቁ የደንብ ማስከበር ኦፊሰር አመራርና ሰራተኛ መፍጠርና መገንባት ላይ በትኩረት መሠራት እንዳለበት አንስተዋል ለዚህም ከተማችን የደረሰችበት የእድገት ደረጃ የሚሸከም  አደረጃጀት የመፍጠር ስራ በልዩ ትኩረት በየወቅቱ በስትራቴጂክ አመራሩ እየተመራ በፍጥነት እንዲተገበር አቅጣጫ ሰጥተዉ፤

በክፍለ ከተማና  በወረዳ ደረጃ  ጀምሮ በሰላምና ጸጥታና ደንብ ማስከበር ተቋሞቻችን የሚታዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር አስተሳሰቦችና ድርጊቶች የተደራጀ የስነ ምግባር ስርጸት ስራየመስራትና ተጠያቂነት የማስፈን ስራ በልዩ ትኩረት በየወቅቱ የግምገማና የክትትል አካል ተደርጎ መሰራት እንዳለበት በማሳሰብ  በከተማችን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና የደንብ ጥሰቶች እንዲቀንሱ በሁለቱም ተቋማት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረዉ በመቀጠል የአገልግሎት አሰጣጥን የተቀላጠፈ በማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ ፈጥሮ  አገልግሎቶችን በቴክኖሎጅ በማስደገፍ መስራት እንደሚገም አንስተዋል።

ሀላፊዋ አክለዉም የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ የከተማችን ሰላም የማፅናት ጥረትን ለማስቀጠል ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ስራ የበለጠ ማጠናከር፣የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ትኩረት መስጠት፣የፅንፈኞችና የሽብር ኃይሎችን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት በመከታተል እርምጃ መዉሰድ፣ የደንብ ጥሰቶችን የማረም ስራ፣ የባለድርሻ  አካላት ሸገር ሲቲን ጨምሮ ቅንጅት ማጠናከር፣ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በትብብር መስራት፣የሰላም እሴት ግንባታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ መፍታት፣ የደንብ ጥሰቶችና ህገወጥ እርድ መከላከል፣የጥምቀት በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ማድረግና መሠል ተግባራት ላይ አመራሩ ተናቦና አጽንኦት ሰጥቶ በቅንጅት መስራት የቀጣይ የርብርብ ማእከል መሆን እንዳለበት አመላክተዋል።

በግምገማ መድረኩ  ላይ የሁለቱም ተቋማት ቢሮ ኃላፊዎች ምክትል የቢሮ ሀላፊዎች እና ዳሬክቶሬቶች ተሳትፈዋል ።