ችግኞቹን የመንከባከብ መርሃ-ግብር
"ተክሎች ልክ እንደ ልጆች ሁሉ እንክብካቤ የሚሹ በመሆኑ በዘላቂነት መንከባከብ ይገባል"
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
***
ጥር 02/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2017/8 የክረምት የ7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የግሪን ሌጋሲ ጥሪ ተቀብሎ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቆሬ አከባቢ የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፉ ይታወሳል።
በዛሬዉ እለትም የቢሮዉ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ምክትል የቢሮ ሀላፊዎች፣የየክፍለ ከተማና የወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የሰላም ሰራዊት አባላት በተገኙበት ችግኞቹን የመንከባከብ መርሃ-ግብር ተካሄዷል።
መርሃግብሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት ኃላፊዋ በንግግራቸው መላዉ የጸጥታ መዋቅር እንደ ጸጥታ ሁሉ በልማት ስራዎችም ፊት አዉራሪ በመሆን ሰፊ ስራ ሲሰራ እንደቆየ በማንሳት በየ ብሎኩና በየ መንደሩ የአረንጓዴ አሻራ ትግበራን ወደ ተግባር የተገባ በመሆኑ የተተከሉ ችግኞች ለፍሬ እንዲበቁ መንከባከብ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለዉም በከተማችን የመትከል ሁኔታ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የጸጥታ መዋቅሩ የግንባር ቀደም ሚናነትን መወጣት እንዳለበት በማመላከት በችግኝ እንክብካቤ መርሃግብሩ መጽደቅ ያልቻሉትን እግረ መንገድ በሌላ ችግር የመተካት ስራ ለመስራት እንደሆነ አዉስተዉ ተክሎች ልክ እንደ ልጆች ሁሉ እንክብካቤ የሚሹ በመሆኑ በዘላቂነት መንከባከብ እንደሚገባ አንስተዋል።
በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አውስተዋል።