የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ አካሄዱ።

         *
ጥር 02/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠሪ ተቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በጋራ በመሆን ከማእከል እስከ ወረዳ ካሉ የተቋማቱ የክ/ከተማና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ዳይሬክቶሬቶች በተገኙበት  የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት  የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግመዋል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት  የአዲስ አበባ ከተማ ሰለምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ  ዘላቂ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት በመሆኗ በበጀት አመቱ አጋማሽ በርካታ የአደባባይ ኩነቶች በርካታ ልማቶች እየተፈጸሙ ዜጎቿ በሠላም ወጥተዉ የሚገቡባት መሆኗን አረጋግጣ ከተማ አቀፍና አገር አቀፍ ሁነቶች ኮንፈረንሶችና የአደባባይ በአላት እንዲሁም በቅርቡ ያሳለፍነዉን የአእላፋት ዝማሬን ጨምሮ ለከተማዋ ተደማሪ የህብረብሔራዊ አንድነትና የወንድማማችነት እሳቤ አይተን ያለፍንባቸዉ ነዉ ሲሉ አዉስተዋል።
 
ኃላፊዋ አክለዉም በከተማዉ የሚስተዋሉ ለዉጦችን ዘላቂነት ለማጽናት የሚያስችሉ ትልልቅ ስራዎች የተሠሩ መሆኑን በዝርዝር ያነሱ ሲሆን ህዝብን አሳትፈን በመስራታችንና የሰላም ሰራዊትን ጨምሮ በተፈጠሩ ጠንካራ አደረጃጀቶች በመታገዝ የስምሪት አግባብን በማስፋት የሚወርዱትን ተልእኮዎች ሳይሸራርፍ የሚተገብር አመራር በመኖሩ በበጀት አመቱ ጥሩ እንቅስቃሴ መኖሩን በማመላከት ከፊታችን የሚጠብቁን የጥምቀትና 7ኛዉ ሃገራዊ ምርጫን ጨምሮ ከጸጥታ ተቋሙ ብዙ ስራ የሚጠበቅ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንዲሰራ አሳስበዋል።

በመድረኩ የሁለቱም ተቋማት የ6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፤በሪፖርቶቹም በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት የጸጥታ መዋቅሩ በጥምር ሀይል በመገምገምና ጥብቅ ስምሪት በመስጠት እንዲሁም ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ የተሠሩ ስራዎች፣በከተማዉ የተካሄዱ አለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች ያለምንም የጸጥታ ስጋት  ዓላማቸዉ ላይ ብቻ  ትኩረት ተደርጎ መሠራቱ፣ በመዲናዋ የተካሄዱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ህዝቡ የሰላም ባለቤት በማድረግ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ በ6 ወራት ዉስጥ የተሠሩ ስራዎች ሲሆኑ፣ ህገ ወጥ የጎዳና ንግዶችን ለማስቀረት የተኬደው ርቀት፣አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባር፣ ወንጀል ጠል የሆነ ማህበረሰብ እንዲኖሩ የተሰሩ ስራዎች፣የኮሪደር ልማት ላይ የሚደርሱ ብልሽቶችን መቆጣጠርና  መሠል በከተማዉ ሰላምን አስፍኖ የህግ የበላይነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ አብይና አበይት ተግባራት በተቋማቱ ሪፖርት ላይ በስፋት ተነስቷል።

የዉይይት መድረኩን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና  የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሲሆኑ፤በቀረቡት ሪፖርቶችና ከመድረኩ ከተሠጡት የመወያያ አጀንዳዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ሀሳብና ጥያቄዎች ተነስተው ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ በሠጡበት ወቅት እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ ዉጤታማ ተቋም ለመገንባት በርካታ ስራዎች ስለመስራታቸዉ አንስተዉ በሰላምና ጸጥታ በኩል የሰላም ሰራዊት ስልጠናና ስምሪትን እንደ አብነት ያነሱ ሲሆን በስነምግባር የታነጸ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ባለስልጣኑ ከከተማ ወጥተዉ በስልጠና የበቁ የደንብ ማስከበር አባላት እንዲፈጠር በበጀት አመቱ ስልጠና መስጠቱን ገልጸዋል።

ስራ አስኪያጁ አክለውም በከተማችን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና የደንብ ጥሰቶች እንዲቀንሱ በሁለቱም ተቋማት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረዉ በመቀጠል የአገልግሎት አሰጣጥን የተቀላጠፈ በማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ ፈጥሮ  አገልግሎቶችን በቴክኖሎጅ በማስደገፍ ከተማችንና አለም በደረሰችበት የቴክኖሎጂ ልክ አገልግሎት ለመስጠት በሁለቱም ተቋማት ወደ ተግባር የተገቡ ስራዎችና በጅምር ላይ የሆኑ ተግባራትም እንዳሉ  አንስተዋል።

የማጠቃለያ ዉይይትና የቀጣይ አቅጣጫ የሰጡት ወ/ሮ ሊዲያ በበኩላቸዉ በተነሱት አጀንዳዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ አድርገዉ የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ የከተማችን ሰላም የማፅናት ጥረትን ለማስቀጠል ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ስራ የበለጠ ማጠናከር፣የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ትኩረት መስጠት፣የፅንፈኞችና የሽብር ኃይሎችን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት በመከታተል እርምጃ መዉሰድ፣ የደንብ ጥሰቶችን የማረም ስራ፣ የባለድርሻ  አካላት ሸገር ሲቲን ጨምሮ ቅንጅት ማጠናከር፣ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በትብብር መስራት፣የሰላም እሴት ግንባታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ መፍታት፣ የደንብ ጥሰቶችና ህገወጥ እርድ መከላከል፣የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ማድረግድግ መሠል ተግባራት ላይ አመራሩ ተናቦና አጽንኦት ሰጥቶ በቅንጅት መስራት የቀጣይ የርብርብ ማእከል እንዲሆን በአደራ ጭምር አሳስበዋል።