በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፤
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፤
ጥር 04/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
**
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማእከል እስከ ወረዳ የተወጣጡ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ፈጻሚዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።
ለውይይት መነሻ የሚሆን ሪፖርት የዘርፉ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ልቅናው ታሪኩ የቀረበ ሲሆን፣በገለጻቸውም የሪፖርቱ አፈጻጸም ግምገማ ዋና ዓላማ የማህበረሰብ አቀፍ የሰላምና ፀጥታ ተሳትፎ እና የአደረጃጀቶች ግንባታና ስምሪት በማጎልበት የህዝቡን የሰላም ባለቤትነት ማረጋገጥ፣የማህበረሰብ የምክክር መድረኮች በማስተባበር የማህበረሰብ የፀጥታ አጠባበቅ ተግባራዊ በማድረግ የማህበረሰብ ተኮር ውይይት ተሳትፎ ማሳደግ እንደሆነም ገልጸዋል።
የዚህ ሪፖርት ግምገማ አስፈላጊነት በዘርፉ የ2018በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብና በማስገምገም ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንደ እጥረት የታዩትን ለቀጣይ እንደ መነሻ በመውሰድ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀጠል ውጤታማ አፈጻጸም ለማምጣት መስራት አና የማህበረሰብ የሰላምና የፀጥታ ተሳትፎና አደረጃጀቶች ግንባታና ስምሪት በማጎልበት፣ወቅቱን የጠበቀ ዕቅድ ለማዘጋጀት የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱን በማቀድ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሆነም አብራርተዋል።
አክለውም አቶ ልቅናው የድጋፍና ክትትል ስርዓት ማጠናከር በቀጣይ የሚከበሩ ሃይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላትን ትኩረት በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላትና ማህበረሰብ ጋር በመስራት አስተማማኝ ሰላም በመፍጠር በዓላቱ ያለምንም ኮሽታ እንዲከበሩ ማድረግ፣ወጣቶችና ሴቶችን ለተሻለ መልኩ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ማሳተፍ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ በሪፖርቱ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በሪፖርት ግምገማው ላይ በመገኘት፣ስራችንን በአግባቡ ለመስራታችን ማሳያ ከሆኑት ውስጥ ህብረተሰቡ በሰላም ወቶ እንዲገባ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉ ማስቻሉ የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት በየግዜው አቅሙን ማደራጀታችን አጥፊዎች ተደብቀው የሚሸሸጉበት ከተማ ሳይሆን እጅ ከፍንጅ የሚያዙበት የጸረ ሽብር ሀይሎችን ሴራ ማክሸፍና መሸሸጊያ አድርገው እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ የተቻለበት የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስና የስጋት ቦታዎችን ቀድሞ በመለየት ከተማዋ ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን የማድረግ ስራ መሰራቱን ሀላፊው ተናግረዋል ።
የማህበረሰብ አቀፍ ውይይትና ምክክሮችን፣በቀጣይ የሚከበሩ የጥምቀት በዓል፣የአፍሪካ ጉባኤ፣ስብሰባዎች በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ የከተማውን ሰላም ማስከበር አጠናክሮ ማስቀጠል ላይም በኃላፊው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቶ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በመድረኩ ላይ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች፣የሰላም ሰራዊት አባላትና የቅጥር ጥበቃዎች ተገኝተዋል።