የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ ሰራተኞች ጋር የ6ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ ሰራተኞች ጋር የ6ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።

  ጥር 06/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                 ****

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ከማእከል እስከ ወረዳ የተወጣጡ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ፈጻሚዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውይይት አደረገ።

ለውይይት መነሻ የሚሆን ሪፖርት  በአቶ ማስረሻ ሀብቴ የቀረበ ሲሆን፣በገለጻቸውም በሪፖርቱ በአፈጻጸም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችና ድክመቶችን በማንሳት በዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን፣ያጋጠሙ ችግሮችን ማየትና የተወሰደ መፍትሔዎችን እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት ሊደረጉባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በሪፖርቱ አቅርበዋል።

 አቶ ማስረሻ አክለውም ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በማሳተፍ የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅና ቀጣይ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ እኩይ ተግባራትን ህግ የማስከበርና የማስጠበቅ ስራ መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን አበራ በሪፖርት ውይይት ላይ በመገኘት፣በዚህ ስድስት ወራት ላይ በጥንካሬ የታየውን አጠናክሮ ማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በማረም፣እንዲሁም ሊፈቱ የሚችሉ  የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በመፍታት የከተማዋን አስተማማኝ ሰላምና ደህንነቷን በጋራ በመስራት ማስጠበቅ እንደሚገባም ተናግረዋል ። 

በመድረኩ ላይ አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪን ጨምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ተገኝተዋል።