ቢሮዉ ያሰለጠናቸውን 6ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮዉ ያሰለጠናቸውን 6ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ

ቢሮዉ ያሰለጠናቸውን 6ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ

        ጥር 07/2018 ዓ.ም(አዲስ አበባ)

                     *****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በንድፈ ሐሳብና በመስክ  ያሰለጠናቸውን 6ኛው ኮርስ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላት በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታድየም በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

የምርቃት መረሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት መልክት ያስተላለፉት ኮምሽነር ጌቱ አርጋው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የ6ኛ ዙር እጩ የሰላም ሰራዊት በንድፈ ሃሳብና አካላዊ ብቃት በማሰልጠኑ በማብቃታቸው በአዲስ አበበ ፖሊስ ስም በማመስገን፤ህዝቡና የሰላም ሰራዊት በመቀናጀቱ በርካታ ሁነቶች፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በአላት በሰላም ተከብሮ እንዳያልፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ኮምሽነሩ አክለዉም የከተማችን ዋነኛ የሰላም ዘብ የሆነው የሰላም ሰራዊት  አሰልጥኖ እንዲመረቅ ማድረግ ከፀጥታ አጠባበቅ ስራ ጎን ለጎን በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣በጋራ አጀንዳ ላይ መግባባትና የህዝቦችን ትስስር በመፍጠር አንድነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር ዓላማው ያደረገ ታላቅ ተግባር ነው በማለት ከፊታችን የሚጠብቁን የጥምቀት በዓልን ጨምሮ ሌሎች ከተማ አቀፍ ሁነቶችን በሰላም ለማሳለፍ ከብሎክ ጀምሮ  በመደራጀት የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር  በመናበብ ከተማዋ የሰላምና ልማት ምሳሌ እንድትሆን በቅንጅት እንዲሰሩ በአደራ መልክ መልእክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው  አዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማት አማካኝነት በሁለንተናዊ መልኩ እየተቀየረች መሆኑን አንስተዉ የተጀመረዉ የማያቋርጥ  ልማትና ለዉጥ የተሳለጠ እንዲሆን  አስተማማኝ ሰላም ወሳኝ ነዉ በማለት አዲስ ተመራቂ የሰላም ሰራዊት አባላት ከነባሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር ተሰናስለዉ የአካባቢያቸውን የከተማቸዉን ሰላም እየጠበቁ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን በዛሬዉ እለትም  22,000 አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አበላት የፀጥታ አጋዥ ኃይል  እንዲሆኑ የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በማጠናቀቅ አደረጃጀቱን በሰው ኃይል በማጠናከር ህብረተሰቡን የሰላሙ ባለቤት ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም  የሚያሳይ ነው ካሉ በኋላ የከተማው ሰላምና ልማት እንዲጠበቅ የፀጥታ መዋቅሩንና ነዋሪውን በማሳተፍ በህግ ማቀፍ የተደራጀ የሰላም ሰራዊት በከተማዋ ሰላምና ደህንነት አይተኬ ሚና እየተጫወተ እንደሆነም አበክረው ገልጸዋል።

በመጨረሻም በከተማችን ከፊታችን የከተራና የጥምቀት በዓል የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ፣7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ፣ኮፕ 32ን ጨምሮ ሌሎች በዓላትና የአደባባይ ሁነቶች ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ኮንፈረንሶችን ሰላማዊ በማድረግ በሀገር ፍቅርና አብሮነት አርያ ከሆነ ነባር የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር በመቀናጀት የጸጥታ ስጋቶችና ችግሮችን ለጸጥታ ሀይሉ መረጃ በመስጠት በንቃት አኩሪ ተግባራችሁን እንድትወጡ ሲሉ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮምሽነር ጌቱ አርጋው ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ዋና ሥራ አስኪያጅና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የማዕከል ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና የየ ክፍለ ከተማዉና የየወረዳዉ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።