በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የከተራና የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከተለያዩ የጸጥታ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የከተራና የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከተለያዩ የጸጥታ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አካሄደ።
ጥር 8/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የከተራና የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከተለያዩ የጸጥታ አካላት ጋር በዓሉን አስመልክቶ ውይይት አካሄዷል።
የውይይቱ ዓላማ በሚቀጥለው ሳምንት እንደ ሀገር በደመቀ ሁኔታ የሚከበረውንና የከተራና የጥምቀት በአል ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን አጉልቶ ለአለም ህዝብ የምናሳይበት ሀገር በአለም አይን ደምቃ የምትታይበት ከመሆኑ ጎን ለጎን ያለ ምንም የጸጥታ መደፍረስ ሳይከሰት በተቀናጀ መልኩ በመስራት የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅና በዓሉ በሰላም እንዲከበር ለማድረግ መሆኑን ለጸጥታው አደረጃደቶች ገለፃ ያደረጉት አቶ ልቅናው ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ናቸው።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ መድረኩን በመሩበት ወቅት እንዳሉት ከፊታችን የሚከበረው ሀይማኖታዊ በዓል የሆነው የከተራና የጥምቀት በዓል ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቢሆንም በዓሉን ለማክበር ከውጭና ከሀገር ውስጥም በርካታ ቱሪስቶች የሚታደሙበት የሀገርን ገጽታ ለማስተዋወቅ ትልቁን ዕድል የሚከፍት መሆኑን በማንሳት
ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ገጽታን በማስተዋወቅ የዕምነቱ አስተምህሮት በሚፈቅደው መንገድ ማክበር እንደሚገባና በሌላ በኩል ደግሞ የሀገርን ገጽታ ለማጠርሸት እዚም እዛም የሚሉ የሽብር የጽንፍ ሀይሎች ሴራን መከታተልና መቆጣጠር ይገባል በማለት ሀላፊው የተናገሩ ሲሆን በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በቅንጅት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ለጸጥታው ስራ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ኮማንደር አጀመ ቤጊ የቦሌ ክ/ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዲቪዚዩን ሀላፊ በበኩላቸው ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ በሚያከብረው በዓል ላይ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በማክበር ጸብ አጫሪ መንገዶችን በሰበቡ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመቃወም በተለይ ደግሞ ወጣቱ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የአንበሳውን ድርሻ በመወጣት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።