የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የፀጥታ ስራዎችን የሰላም ሰራዊት ንቅናቄ ውይይት መድረክ አደረገ።

የጥምቀትና ከተራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት እንደሚገባው ተገለፀ።

   ጥር 09/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                 ****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የፀጥታ ስራዎችን የሰላም ሰራዊት ንቅናቄ ውይይት መድረክ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  በውይይት ላይ በመገኘት፣የጥምቀት በዓል ትውፊቱንና ሃይማኖታዊ ዕሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበርና ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ ሀይል ጋር  መረጃ በመለዋወጥ  እንዲሁም ህብረተሰቡን በማስተባበር የሽብር ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍና የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስና የስጋት ቦታዎችን ቀድሞ በመለየት ከከተራ ጀምሮ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የበኩላቹን ሚና እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም መላው የከተማችን ነዋሪ በህብረት ወጥቶ የሚያከብረው በዓል እንደ መሆኑ ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል የመቻቻልና የመከባበር ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን በጠበቀና ወንድማማችነትና እህትማማችነት በሚያዳብር እንዲሁም የሀገርን ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገነባ መልኩ ያለምንም የጸጥታ ችግር ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ከጸጥታው ተቋማት ጋር በመቀናጀት ክብረ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲውል  ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ ሲሆኑ የዚህ የንቅናቄ መድረክ ዋና ዓላማ የ2018 ዓ.ም በከተማችን በድምቀት የሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ከዚህ ቀደም ዝግጅት ጀምሮ ታቦታት እስኪመለሰ ድረስ በዓሉ ትውፊቱንና ዕሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡን ጨምሮ ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።