በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ከ4ሺህ በላይ የሚሆኑ ብሎኮችን ለሚመዝኑ አካላት ኦረንቴሽን እና የስራ ስምሪት ተሰጠ።
በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ከ4ሺህ በላይ የሚሆኑ ብሎኮችን ለሚመዝኑ አካላት ኦረንቴሽን እና የስራ ስምሪት ተሰጠ።
ጥር 19/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
**
የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ከ4ሺህ በላይ የሚሆኑ ብሎኮችን ለሚመዝኑ የዘርፉ የክ/ከተማ አስተባባሪዎች እና ለተመረጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት ሰጥቷል።
በስራ ስምሪቱ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በከተማው ውስጥ የሚገኙ ብሎኮች በሙሉ አሁን ላይ ያሉበትን ሁኔታ ከማወቅና ከመረዳት ብሎም ምቹ ሁኔታቸውን በደንብ አውቆ ከመረዳት አንጻር አልፎም የጸጥታው አጠባበቅ የአካባቢው ጥበቃ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች ምን እንደሚመስሉና ህብረተሰቡ በየአካባቢው በመወያየት ምን አክል ችግሮችን በመፍታት እርስ በእርስ ከመግባባት አልፎም ሰላምን እንዴት መገንባት እንደሚችሉና አካባቢያቸውን ከመጠበቅ አንጻር አሁን ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጽ ስራዎችን ተግባራዊ ያደረገ ስራ ነው የምንሰራው በማለት የተናገሩ ሲሆን
ኃላፊው አያይዘውም መዛኙ ቡድን ስራዎችን በአግባቡ በመስራት ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎች በተሰጠው መስፈርት መሰረት የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀትና ስምሪቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ስምሪቶቹ በሙሉ በትክክለኛው መንገድ ተግባራዊ በማድረግና ሀላፊነታቸውንም በተገቢው መንገድ እየተወጡ እንደሆነ ማህበረሰብ አቀፉ ውይይቶችና ያመጡት ለውጥ ብሎኮቹ ከሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም ከአዋኪ ድርጊት የጸዱ ለእይታ ሳቢ ስለመሆናቸውና ሌሎችም በተቀመጠው መስፈርት ልክ እየተከናወኑ ከመሆናቸው አንጻር መረጃዎችን በመሰብሰብ ደረጃም በማውጣት ስራውን በፍጥነት በጥራትና በታማኝነት በመስራት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።
ስለ ምዘናውና የስራ ስምሪቱን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉት ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ሰራዊት የጸጥታ አደረጃጀቶችና ማህበራት ግንባታ ስምሪትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ገለጻ ካደረጉ በኋላ ከመዛኞቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል ።