የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የልምድ ልውውጥ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የልምድ ልውውጥ አካሄደ።
20/05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አንድ በሚያደርጋቸው የኮሙኒኬሽን አግባቦትና የህዝብ ግንኙነት የስራ ዘርፎች ላይ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል።
በልምድ ልውውጡ ላይ ስለ ደንብ ማስከበር የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ስለ ተቋሙ ተግባር፣ሀላፊነትና ብሎም ስለ ኮሙኒኬሽኑ ዳይሬክቶሬት ስለ ስራ ክፍሉ
መዋቅር፣ አደረጃጀቶች እና ሌሎችም ዝርዝር ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል።
ተቋሙም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቱም ከተቋቋመ አጭር አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ከባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኖቹ ጋር በስራዎቻቸው ዙሪያ መግባባት ላይ በመድረስ መሰራት በመቻሉ የተሻለ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የተቋሙን የገፅታ ስራዎች በመገንባት የህብረተሰቡን ዕይታና እሳቤ መቀየር መቻሉንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
በተቋሙ ውስጥ የድምፅና የምስል ስቱዲዮ አስገንብቶ በማስመረቀ ብሎም ስራ ላይ በማዋል የኮሙኒኬሽኑም ባለሙያዎች እራሳቸውን ከግዜ ወደ ግዜ አቅማቸውን እየገነቡም እንደሚገኙ በመግለጽ ከበርካታ የህብረተሰብና የሚዲያ አጋሮችም ጋር በትብብርና በቅንጅት በመስራት ተደራሽነቻቸውንም ማስፍት እንደቻሉ ዳይሬክተሩ በመጠቆም ስራዎችን ለመስራት በርካታ ችግሮች ቢገጥሟቸውም አሁን ላይ የተሻለ ስራዎችንም ለመስራት አቅም እንደፈጠረላቸው ጭምር ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በተጨማሪ የልምድ ልውውጥ ሊያደርጉ ከመጡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች በተጨማሪ ፣የአዲስ አበባ ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ጋር በመሆን ስለ ህዝብ ግንኙነት፣ሚዲያ ሞኒተሪንግ፣ዶክመንተሪ አጫጭር ፕሮግራሞች ስፖትና የፕሮዳክሽን ስራዎችና ሌሎችም ሞያዊ ስራዎች ላይ በበቂ ሁኔታ ተሞክሮዎችን በጋራ በመወያየት ለሀገርና ለህብረተሰቡ ተቋማችን የሚመጥን መረጃ ተደራሽ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩን አላማ ከግብ በማድረስ ሰፊ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጭምር ሰፊ ውይይቶችም ለማድረግ ችለዋል።