በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በ6ወራት ውስጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በ6ወራት ውስጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።
ጥር 27/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው እንደገለጹት፣በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በዋናነት በተመረጡ ጉዳዮች ላይ የስልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች፣ኮንፈረንሶችን በማካሄድ፣ከብሔራዊ በጎ ፍቃድ ጋር ተያይዞ በሰላም ሚኒስቴር በኩል ሰልጥነው የመጡ ወጣቶችን በመቀበል ለብሔራዊ መግባባት ያለውን አስተዋጽኦ በማበርከት እና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ በመሆን የክትትልና ድጋፍ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።
አቶ ሙሉቀን በተለይም በአዲስ አስተሳሰብና እይታ የሴቶች የወጣቶች፣የአካል ጉዳተኞች፣ከሃይማኖት
አባቶች፣ከታዋቂ ግለሰቦች፣አባገዳዎች፣ሃደ ስንቄዎች፣እድር ምክር ቤቶች እና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ኮንፍረንስና ስልጠናዎችን በማካሄድ እንዲሁም ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች "ኪነ-ጥበብ ለሰላም" በሚል ፓናል ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በዘርፉ በተለይም በከተማችን ብዙ ተከታይ ያላቸውን ቲክቶከሮች ወይም አክቲቪስቶች ጋር መድረክ በመፍጠር በሰላም ዙሪያ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ውይይት ማድረጋቸውንና ከተለያዩ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ወደ ተግባር እያስገባ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ከብሔራዊ በጎ ፈቃድ ጋር ተያይዞ የቤተሰብ ትስስር የመፍጠር እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ደግሞ ለተመረጡ ተማሪዎች የቃልኪዳን ቤተሰብ ትስስር በመፍጠር ስራዎች ተሰርቷል።
ከክትትልና ድጋፍ ጋር ተያይዞ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሕጋዊነታቸውን የማረጋገጥ፣የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አደረጃጀት የተጓደሉ ቦታዎችን እንዲሟሉ ድጋፍ የማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን እንዲፈቱ ጥረት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።
አቶ ሙሉቀን አክለውም ሌሎች በርካታ ስራዎችን መስራታቸውንና በከተማዋ ላይ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍንና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ መቻሉንም ከተቋም ጋር በቅንጅት ስራዎችን እንዲሰራ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።