ቢሮው የጋራ መኖሪያ እና የማህበር ቤቶች አከባቢ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመቀነስ የሚያስችል ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።
ቢሮው የጋራ መኖሪያ እና የማህበር ቤቶች አከባቢ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመቀነስ የሚያስችል ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።
ጥር 30/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ በከተማዋ ውስጥ ለሚገኙ የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ባለቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ እና የማህበር ቤቶች ሰብሳቢዎች የወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር የተመረጠ ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ ላይ በከተማዋ ውስጥ በጋራ መኖሪያ እና በማህበር ቤቶች አካባቢ የሚከሰቱ የፀጥታ ግኝቶች፣ የወንጀል መከላከል ዘዴዎች፣ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ሚና እና ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር የሚደረግ ትብብር በስፋት ተነስቷል።
የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ል የቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ከተማችን በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን ጠቁመው፣የህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የፀጥታ አካላት ተግባራዊ ትብብር በማድረግ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
በግምገማዊ ስልጠና የተገኙ ግኝቶችን በሰነድ መልክ ያቀረቡት የቢሮው የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የማህበረሰብ አቀፍ እና የተቋማት ደህንነት፣ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዳምጠው አያሌው ሲሆኑ በገለጻቸው ላይ የተከናወኑ የፀጥታ ድጋፍና ክትትል ስራዎች የተገኙ ግኝቶችን አብራርተው፣በቀረበው ሪፖርት ላይም የተሻሉ አፈፃፀሞችን ለማጠናከር እና የታዩ ጉድለቶችን ለመሙላት አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ልምዳቸውን የተጋሩበት ሲሆን፣ በቀጣይ ጊዜ በተቀናጀ መልኩ የፀጥታ እና ደህንነት ስራዎችን ለማጠናከርና በጋራ መስራት እንደሚገባ ተወያይተው፣ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የሚሆኑ ጉዳዮችንም አስቀምጠዋል።
የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ል የቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ፣ኮ/ር ገዛኸኝ ጌታለም የአ/አ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር፣ረዳት ኮ/ር አለማየሁ አያልቄ የአ/አ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክተር፣የ11ዱም ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ኃላፊዎች የጋራ መኖሪያ እና የማህበር ቤቶች የፀጥታ ዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመድረኩ ተገኝተዋል።